የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ከዐረብ ባንክ የተገኘው ብድርና የፋይናንስ ድጋፍ በሥራ ዕድል ፈጠራ በመታገዝ ኢኮኖሚውን ለማሳለጥ የጎላ ሚና ይጫወታል-ተስፋዬ በልጂጌ( ዶ/ር)

Jun 4, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 26/2017(ኢዜአ)፦ከዐረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት የተገኘው ብድርና የፋይናንስ ድጋፍ በሥራ ዕድል ፈጠራ በመታገዝ ኢኮኖሚውን ለማሳለጥ የጎላ ሚና እንደሚጫወት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ( ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን፤ የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡


ከነዚህም በኢትዮጵያና በዐረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት መካከል ለተቀናጀ ውጤታማ ግብርናና ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት፤ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገው የብድር ሥምምነት ረቂቅ አዋጅ አንዱ ነው።

በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ( ዶ/ር) አዋጁን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ የብድር ሥምምነቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማሳለጥ የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ ባለፈ የሥራ እድል ፈጠራ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆን ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አለው።

የዐረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት 49 ሚሊዮን 550 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በድጋፍና በብድር ማቅረቡን ጠቅሰው፤ ከዚሁ ውስጥ 450 ሺህ ዶላሩ በድጋፍ መልክ የሚቀርብ ነው ብለዋል።

ገንዘቡ በግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ የመስኖ አውታሮችን በማስፋፋት፣የባለሙያ ምክር አገልግሎት በመስጠት፣ ለአስተዳደር ማህበራትና ተቋማት የአቅም ግንባታ ተደራሽ በማድረግ የግብርና ምርታማነትን በሚያሳድጉ ተግባራት ላይ የሚውል መሆኑንም አብራርተዋል።

ስምንት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የመስኖ ቦይ፣ የውሃ ማሰራጫና የውሃ ማቆሪያ መስመሮች ግንባታን ያካተተ መሆኑን ጠቁመው፤ በግብርና ኢንዱስትሪ የምርት ሰንሰለት ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ሌላው ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል።

በሥምምነቱ መሰረት በመጀመሪያው ምዕራፍ 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ፥ በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ 29 ሚሊዮን 550 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ፈሰስ የሚደረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የተገኘው ብድር የአምስት ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ20 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት፤ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አኳያ የገንዘቡ መገኘት ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

ገንዘቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግና፣ ፍትሃዊ ተደራሽነት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።


የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ የተገኘው ፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች በአካባቢያቸው ካሉ አርሶ አደሮች የምርት ግብዓት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል።

አሁን እንደ አገር ባለን አፈጻጸም ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውሉ የፋይናንስና ብድር ድጋፍ እየጨመረ መጥቷል ነው ያሉት።

በተለያየ መልኩ የሚገኙ እገዛዎችን በፍትሃዊነት ተደራሽ ከማድረግ አኳያም በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያና በዐረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት መካከል የተደረገውን ሥምምነት ለማጽደቅ የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

በተመሳሳይም ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለሴቶች እና ልጃገረዶች ጤና የተቀናጀ ጠንካራና በፈጠራና እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የተደረገውን የብድር ሥምምነት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025