
አርባ ምንጭ፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፡- የኦዲት ሥራዎችን ጥራትና ተደራሽነትን በማሳደግ የሀገርና የሕዝብ ሀብትን ከብክነት እየታደገ መሆኑን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ገለጸ።
23ኛው ፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት፣ የዋና ኦዲተሮች እና ባለድርሻ አካላት ዓመታዊ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ የፌደራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ፤ የኦዲት ሥራዎች የሀገርና የሕዝብን ውስን ሀብት ከብልሹ አሠራር እየታደገ ነው ብለዋል።
የኦዲት ሥራዎች በአሠራር፣ በቅልጥፍና፣ በጥራትና በሽፋን ለማሳደግ በተደረጉ ጥረቶች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
የኦዲት ግኝት አስመላሽ ኮሚቴ የሥራና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ፣ የኦዲት አሠራርና አስተዳደር ስርዓት ለማበጀት እንዲሁም የኦዲት ግኝቶች እርምጃ አወሳሰድና የኦዲት ተቋማት ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ ጠንካራ ተግባር ሲፈጸም ቆይቷል ነው ያሉት።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ በበኩላቸው፥የኦዲት ሥራዎች የመንግስትና ህዝብ ውስን ሀብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
የመንግስትና ሕዝብ ሀብትን ከምዝበራ ለማዳን የገቢ አሰባሰብ እና የወጪ ስርአቶችን ከብክነትና ምዝበራ ለማዳን ጠንካራ ተግባር እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በጀትን በፋይናንስ አዋጅ መሠረት ተገቢውን የኦዲት ሥራ እያከናወነ ይገኛል ያሉት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር አቶ አበባየሁ ኤርሚያስ ናቸው።
የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች የበጀት ህጉን በመከተል የህዝቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽ በማድረግ በኩል ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው የጉባኤው መድረክ የፌደራል እና የክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አባላት እና ዋና ኦዲተሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026