ወልቂጤ፤ ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የቀጣናውን ሀገራት አብሮ የማደግ ዕድል ስለሚያሰፋ ለስኬቱ በትብብር መስራት እንደሚገባ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሚሰሩ ምሁራን ተናገሩ።
በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ በቃሉ አንጭሶ(ዶ/ር) እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበራትን የባህር በር ባልተገባ መንገድ አጥታለች።
በዚህም ላለፉት 35 ዓመታት እንደሀገር ብዙ ዋጋ መከፈሉን ጠቅሰው፣ የባህር በር ማጣቷ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ ጫና ሲያሳድር መቆየቱን አንስተዋል።
በተለይ በወጪና ገቢ ንግድ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ሲያሳድር እንደነበር አስታውሰው፣ የለውጡ መንግስት ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ የጀመረው ጥረት ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ማግኘት በቀጣናው የሀገራትን አብሮ የማደግ ዕድል ከማስፋት ባለፈ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ፋይዳው የላቀ መሆኑንም ተናግረዋል።
እንደ ሀገር የተሻለ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የባህር በር መኖር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ በሌሎች ሀገራትም መሰል ጥያቄዎች ተነስተው እንደነበር አስታውሰዋል።
በዓለም አቀፍ የውሃ አካላት አጠቃቀም ስምምነት መሰረት በተለያዩ ሀገራት መሰል ጥያቄዎች ተነስተው ተፈጻሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ለማሳካት መንግስት የጀመረው ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ እውን እስኪሆን ድረስ በጋራ ተባብሮ መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያውያን በያለንበት ስናደርግ የነበረውን እገዛ በቀጣይም አጠናክረን መቀጠል አለብን ነው ያሉት።
ሌላው በዩኒቨርሲቲው የህግ መምህርና ተመራማሪ ተሾመ ሐበሻ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አብሮ የማደግና የመልማት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ነው።
ይህም በአካባቢው ያሉ ሀገራት ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከርና እድገታቸውን ለማፋጠን ፋይዳው የጎላ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የባህር በር ለሌላቸው ሀገራት በአካባቢው ያለውን የባህር በር የመጠቀም ዓለም አቀፍ ስምምነት እንዳለ አስታውሰው፣ ይህም ኢትዮጵያ ላነሳችው የባህር በር ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንድታገኝ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ባልተገባ መንገድ የነበራትን የባህር በር ማጣቷ በአሁኑ ወቅት ለወደብ ኪራይና ለማጓጓዣ በየዓመቱ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ለማውጣት መገደዷን ገልጸው ይህም ለሌላ ልማት መዋል ያለበትን ገንዘብ እያሳጣት መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በር የመጠቀም መብት ያላት በመሆኑ ያነሳችው ጥያቄ ህጋዊ መሰረት ያለው መሆኑንም ነው የህግ መምህሩ ያብራሩት።
የባህር በር ለማግኘት መንግስት የጀመረው ጥረት እስኪሳካ ድረስ ማገዝ ይገባናል ሲሉም አስገንዝበዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025