
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2017(ኢዜአ)፦ የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ሥራ ከፍተኛ የፍሰት ጭንቅንቅ የነበረበትን ከባቢ ቀይሮታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገዶች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች፣ ሱቆች፣ የሕዝብ ማረፊያ ፕላዛዎች፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ የተለዩ የታክሲ እና የአውቶቡስ ቤዮች መሠራት አካባቢውን የበለጠ ተደራሽ፣ አካታች እና ለመኖር ምቹ አድርጎ እንደገና የገነባ ተግባር ነው ብለዋል።
የከተማም ሆነ የገጠር ኮሪደር ሥራዎች የከበረ የሰውልጅ የአኗኗር ዘይቤን ያስተዋወቀ እና ፍትኃዊ የሕዝባዊ ስፍራዎች አጠቃቀምን በመፍጠርም ማኅበረሰቦችን ከፍ ያደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በተለይም በቅርቡ የጀመርናቸው የገጠር ኮሪደር ሥራዎች የገጠር የመኖሪያ ከባቢዎችን እንደገና በማደስ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ያለሙ ናቸው ብለዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራ ወደ ከተማው ጫፎች እንዲደርስ ሀብት በማሰባሰብ የከወኑትን የአዲስ አበባ አስተዳደር እና የክፍለ ከተማ አመራሮችን ከልብ ለማመስገን እፈልጋለሁ ብለዋል።

በከተማችን የሚገኙ ሌሎች ክፍለ ከተሞች እና በመላው ሀገራችን የሚገኙ ከተሞችም የከተማ አኗኗርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በአዲስ ምናብ እና የሀሳብ ውቅር ለመሥራት በተነሳንበት በአሁኑ ወቅት ዜጋ ተኮር የሆኑ ተግባራትን ቅድሚያ ሰጥተው መሥራታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀርባለሁ ነው ያሉት።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026