አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለውጭ ኢንቨስትመንት የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መጠቀም ተገቢ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለ ኢትዮጵያ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ በቂ ግንዛቤ የሚያገኝበት መመሪያ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ዛሬ ይፋ የሆነው "DIPLOMATIC GUIDE FOR THE HOME-GROWN ECONOMIC REFORM AGENDA" በሚል ርዕስ የተሰናዳው መመሪያ ሰነድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።
በተለይም በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲወሰን በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ መጨመሩን ገልጸዋል።
ዛሬ ይፋ የተደረገው የዲፕሎማሲ መመሪያ ሰነድም የኢንቨስትመን ፍሰትን በመጨመር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ያስመዘገበችውን ውጤት ለማላቅ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያን ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መኖር አለበት ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ በተለያዩ ሀገራት ያሉ ሚሲዮኖች ስለኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማነት በኩራት የሚናገሩበት ጊዜ መሆኑን አስረድተዋል።
በመሆኑም በጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሪፎርም እንዲደግፉ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የሚመረቱ ምርቶችን ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች በቀላሉ ማጓጓዝ የሚያስችል እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ የተሳለጡ የትራንስፖርት አማራጮች እንዳሉም ጠቅሰዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ የዕዳ ጫና፣ ከፍተኛ ስራ አጥነት፣ ዝቅተኛ የማምረት አቅምና የፕሮጀክት አፈፃፀም እንደነበረበት አስታወሰዋል።
ይሁን እንጂ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በግብርና ዘርፍ በስንዴ ምርት እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በማሻሻልና ተኪ ምርቶችን በማምረት ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የዕዳ ጫናዋን በመቀነስ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት ተርታ መመደቧን ገልጸው፣ ቀጣይነት እንዲኖረው የኢትዮጵያን አዳዲስ የኢንቨስትመንት አማራጮች በሚገባ ማስተዋወቅ ይገባል ነው ያሉት።
ዛሬ ይፋ የተደረገው የዲፕሎማሲ መመሪያ ሰነድም የኢትዮጵያን እምቅ አቅሞች በማስተዋወቅ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ያስችላል ብለዋል።
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለውጭ ባለሀብቶች የተፈጠሩ እድሎችን በሚገባ የሚያብራራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታና ምቹ የኢንቨስትመንት አቅም በተዘጋጀው መመሪያ ሰነድ አማካኝነት ማስተዋወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025