የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

'ጣናነሽ 2' ጉዞዋን ቀጥላ ዛሬ አዳማ ደርሳለች

Jun 12, 2025

IDOPRESS

አዳማ ፤ሰኔ 4/2017(ኢዜአ)፡- በጣና ሃይቅ ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠትና የቱሪዝም ፍሰቱን ለማሳደግ ታስባ ወደ አገር ውስጥ እየተጓጓዘች የምትገኘው 'ጣናነሽ 2 ጀልባ' አዳማ ከተማ ደርሳለች።

'ጣናነሽ 2' አዳማ ስትገባ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባና የከተማው ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላታል።

ከጂቡቲ ዶራሌህ ወደብ ተነስታ ኢትዮጵያ ጉዞ ላይ የምትገኘው 'ጣናነሽ 2' ከረጅም ጉዞ በኋላ በዛሬው ዕለት ደግሞ አዳማ ከተማ ገብታለች።


'ጣና ነሽ 2' 150 ሜትሪክ ቶን ክብደት ሲኖራት ርዝመቷም 38 ሜትር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከ188 ሰው የመጫን አቅም እንዳላትም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ በተለያዩ ሐይቆች ላይ በዘመናዊ ጀልባዎች የታገዘ የውኃ ላይ ትራንስፖርት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ለዚህም የሚያግዙ ዘመናዊ ጀልባዎችን በማስመጣት በሀገር ውስጥ ሐይቆች ላይ ትራንስፖርትን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ 'ጣና ነሽ 2' ለዚሁ አገልግሎት ወደ መዳረሻዋ ባህር ዳር እየተጓጓዘች መሆኑን ተቋሙ አመልክቷል።

ወደፊትም ላንጋኖ እና ሻላን ጨምሮ በሁሉም ሐይቆች ላይ በዘመናዊ ጀልባዎች የታገዘ የውኃ ላይ ትራንስፖርት ለመስጠት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

የ'ጣና ነሽ 2' ጉዞ የተሳለጠ እንዲሆን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የየክልሎቹ የትራፊክ ፖሊስ አባላት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነም ተገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጀልባዋን ለማሳለፍ በመንገድ ላይ ያሉ የኤሌክትሪክ ገመዶችን በማንሳት እንዲሁም የሚቋረጡ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን በፍጥነት በመመለስ ርብርብ እያደረጉ መሆኑም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025