አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የወጣቶችን ተጠቃሚነት በዘላቂነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የመዲናዋ ወጣቶች ጋር "የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት አካሂደዋል።
ከንቲባዋ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች የሀገር ጉልበትና ተስፋ ናቸው ብለዋል።
መንግስት በምጣኔ ሃብት ያደገችና ለዜጎች ምቹ ሀገርን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህ ውስጥ የወጣቶች ሚና ወሳኝ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በከተማዋ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች፣ በሀገራዊ ፕሮጀክቶችና በዘላቂ ሰላም ግንባታ ሂደት ወጣቶች ጉልህ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የአሁኑ ትውልድ በሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በከተማ ልማት፣ በምግብ ራስን ለመቻልና በሌሎች የልማት ሥራዎች ታሪክ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ወጣቶች በሰው ተኮር፣ በበጎ ፈቃድ፣ ሰላምና ጸጥታ፣ በኮሪደር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶች ጉልህ ሚና በመጫወት የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በውይይት መድረኩ የተሳተፉ ወጣቶች በበኩላቸው በከተማዋ በስራ እድል ፈጠራ፣ በፖለቲካ ተሳትፎ፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ በወጣት ማእከላት ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል።
ወጣቶችን በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ምጣኔ ሃብት ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ አካታች እድገት ለማምጣት የተጀመረው ተግባር የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።
የስራ እድል ፈጠራ፣ የብድር አቅርቦት፣ የመስሪያ ቦታ፣ የሰብዕና መገንቢያ ማዕከላት፣ አማራጭ የቤት አቅርቦትን በተመለከተ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን፥ ወጣቶች ያነሷቸው ሀሳቦችና ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ ተናግረዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታትም ለወጣቶች በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ገልጸዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ፥ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አስረድተዋል።
ባለፉት አሥር ወራት ብቻ 301ሺህ ወጣቶች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ገልጸው፥ በኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ወጣቶች ደግሞ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ብድር መሰጠቱን ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማጠቃለያ መልዕክታቸው በከተማዋ በተገነቡ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት አማካኝነት ወጣቱን አምራች ዜጋ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ወጣቶቹ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ በወንዝ ዳርቻ፣ በኮሪደር ልማትና በመኪና ማቆሚያዎች በተከናወኑ የልማት ስራዎች በፈጠራ በመታገዝ በዘላቂነት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
በምጣኔ ሃብት፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ዘርፎች የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ወጣቶች በክህሎትና በእውቀት ተወዳዳሪ በመሆን ለሀገር ብልፅግና በትጋት መስራት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025