የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኮሪደር ልማቱ ለንግድ ስርዓቱ መሳለጥ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል

Jun 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2017(ኢዜአ)፦በመዲናዋ በመከናወን ላይ ያለው የኮሪደር ልማት ለንግድ ስርዓቱ መሳለጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና የአለም የዲፕሎማቲክ ማዕከል መሆኗን ተከትሎ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ይከናወኑባታል፡፡

አዲስ አበባን በስሟ ልክ ውብ በማድረግ፣ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚመጥን ቁመና ለማላበስና ለነዋሪቿ ምቹ ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሚታይ ውበትና ለውጥ አምጥተዋል፡፡


የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የአንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ፣ የጎሮ አደባባይ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የዚሁ ማሳያ ነው፡፡

ከአንበሳ ጋራዥ እስከ ጎሮ አደባባይ በተሰራው የኮሪደር ልማት ዙሪያ በንግድ ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት የኮሪደር ልማቱ ምቹ የስራ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል።

የኮሪደር ልማቱ አስፈላጊ፣ ወቅቱን የዋጀ እና ለሌሎች ከተሞች በምሳሌነት የሚወሰድ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

በሴቶች አልባሳትና ኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቅ የምትሰራው ወጣት እየሩሳሌም ፀጋዬ ካሁን ቀደም መንገዱ ጠባብ ከመሆኑ ባለፈ ቤቶቹ በቆርቆሮና በሸራ የተሰሩ ስለነበሩ ለንግድ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ እንደነበሩ ነው የገለፀችው።


የካፌ ባለቤት የሆኑት አቶ አዳነ በሪሁን በሰፈሩ ለረጅም አመታት መስራታቸውን ገልፀው ቀደም ሲል በአካባቢው የፍሳሽ ማስወገጃ ስላልነበር ስራቸውን አስቸጋሪ አድርጎባቸው እንደነበረ አስታውሰዋል።

የየረር ፋርማሲ ባለቤት ወይዘሮ አስቴር አድማሱ እንዳሉት የትራፊክ መጨናነቅና የተበላሹ መንገዶች በንግድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ጫና ሲያሳድሩ ቆይተዋል።


የኮሪደር ልማቱ ይህን ችግር በመፍታት ምቹ የመንቀሳቀሻ ስፍራ በመፍጠር ሸቀጦችን እንደልብ ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር የሚረዳ እንደሆነ እምነታቸውን ገልጸዋል።

በአዋቂዎች አልባሳት ሽያጭ የተሰማሩት አቶ ሀይረዲን ሱልጣን በበኩላቸው ቦታው ካሁን ቀደም ለስራ የማይመች፣ አስቸጋሪና የተጨናነቀ እንደነበር አስታውሰው ለውጡ ከፍተኛ መሆኑን ነው የገለፁት።

የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ ነዋሪ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣቱን በመናገር የመኪና እና የእግረኛ መንገዶች ስፋትና ውበት አካባቢውን በብዙ መልኩ የለወጠና ነዋሪውን ያስደሰተ መሆኑን ነጋዴዎቹ ገልፀዋል።


በመዲናዋ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ውብ ከማድረጉ ባለፈ የንግድ ስርዓቱን በማሳለጥ የንግዱ ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉን ወጣት እየሩሳሌም ፀጋዬ ፣ አቶ አዳነ በሪሁን እና ወይዘሮ አስቴር አድማሱ አንስተዋል።



በተለይም በንግድ ስራ የተሰማሩ አካላት እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ እንዲሰሩ መደረጉ አዲስ የስራ ባህልን ለማዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አቶ ነስሩ ሱልጣንና አቶ ሀይረዲን ሱልጣን ተናግረዋል፡፡።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025