
አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገነባው ሶላር ፕሮጀክት ለተቋሙ ሀይልን ከማቅረብ በዘለለ የሶላር ሀይልን አመንጭቶ ወደ ዋናው ግሪድ የሚያስገባ ማሳያ ፕሮጀክት ነው ሲሉ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር 100 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ የመጀመሪያውን የሶላር ፕሮጀክት በተቋሙ ጊቢ ውስጥ አስመርቆ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱን መርቀው ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት በአገሪቱ የሀይል ማመንጨት አቅምን ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በዚህም በአገሪቱ ስድስት ነጥብ ስምንት ጊጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ላይ መድረስ የተቻለ ሲሆን ከሶላር ኢነርጂ ወደ 10ሺ የሚጠጋ ሃይል በማመንጨት ማህበረሰብን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
የሀይል አቅርቦትን ከማሳደግ አንጻር ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን ያነሱት ሚኒስትሩ በቀጣይም የሀይል አቅርቦትን የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በሚኒስቴሩ ግቢ ውስጥ የተገነባው 100 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክት የሶላር ኢነርጂን በከተማ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ማሳያ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የተገነባው ሶላር ፕሮጀክት ተቋሙ የሚፈልገውን ሀይል ተጠቅሞ ቀሪውን ወደ ዋናው ግሪድ የሚያስገባና ሌሎች ሊከተሉት የሚገባ ምሳሌ የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡
በተለይ ባለሀብቶች የተለያዩ ተቋማት የውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የጀመረውን ተሞክሮ በመውሰድ ተግባራዊ ቢያደርጉ ለሀይል አቅርቦት ማደግ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንም አመላክተዋል።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የታዳሽ ሀይል ማመንጨት የሚችል እምቅ አቅም እንዳላት አስታውቀዋል፡፡
ይህን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ በዚህም በገጠር አካባቢዎች፣ በጤና ተቋማትና በትምህርት ቤቶች ያለውን የመብራት ሀይል ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
መሰል የሶላር ኢነርጂ ፕሮጀክቶችን የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች ቢጠቀሙ የአገሪቱን ኢነርጂ ፍጆታ መሸፈን የሚያስችል በመሆኑ በቀጣይ ሊሰራበት ይገባልም ብለዋል።
በቀጣይ ተቋማት የሶላር ኢነርጂ እንዲጠቀሙ ግንዛቤ መፍጠር እንዲሁም በህግ በማስደገፍ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የተገነባው የሶላር ኢነርጂ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ ሶላር አልያንስ ጋር በመተባበር እንደሆነም ተመላክቷል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026