
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2017(ኢዜአ)፥ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የቆዳ ኢንዱስትሪው እንዲነቃቃ ማድረጉን የቆዳ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል አስታወቀ።
የቆዳ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ዙልፍካር አባጅሐድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በንቅናቄው በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የቆዩ ስድስት ኩባንያዎች በተደረገላቸው ድጋፎች ወደ ምርትና ውጭ መላክ ስራዎች ተመልሰዋል።
የተኪ ምርት ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ በመተገብሩም ለጸጥታ አካላትና ለተለያዩ ተቋማት ለስራ የሚውሉ ከቆዳ የሚዘጋጁ ጫማዎች ሙሉ ለሙሉ በአገር ውስጥ አምራቾች እየቀረበ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በ2017 በጀት ዓመት አስራ አንድ ወራት ብቻ 196 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው የቆዳ ምርት በአገር ውስጥ በማምረት ከውጭ የሚገባውን መተካት መቻሉን ገልፀዋል።
የአገር ውስጥ የቆዳ ምርቶች ጥራት፣ ዲዛይንና ስብጥር በመሻሻሉ የማህበረሰቡ አመለካከትና አጠቃቀም እያደገ መምጣቱን ተናግረው በመዲናዋ የሚዘጋጁ አለም አቀፍ ሁነቶች የቆዳ ውጤቶችን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው ብለዋል።
የጥሬ ቆዳና ሌጦ የጥራት ችግሮችን ለመፍታት ከእርድ ጀምሮ እስከ ፋብሪካ ድረስ ያሉ ተዋናዮች ላይ የሚታዩ የክህሎት ክፍተቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደተሟላ ትግበራ ከመግባቱ በፊት ለቆዳ ምርት አስፈላጊ ኬሚካሎችን ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ተግዳሮት እንደነበረ አውስተዋል።
አሁን ላይ ማሻሻያው ተግባራዊ በመሆኑ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በመሻሻሉ ግብአቱን ከውጭ ለማስገባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
የቆዳ ፋብሪካዎች ከውሃ ፣ከኬሚካልና ሌሎች ሀብቶች አጠቃቀም፣ ከሠራተኞች አያያዝና ደህንነት መጠበቅና ሌሎች መስፈርቶች አንጻር ማሟላት ያለባቸው አለም አቀፍ መስፈርቶች እንዳሉ ተናግረዋል።
‘ሌዘር ወርኪንግ ግሩፕ’ የተሰኘ አለም አቀፍ ድርጅት በየዓመቱ የቆዳ ፋብሪካዎችን ኦዲት በማድረግ የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል ብለዋል።
ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ማረጋገጫውን ያገኘ ድርጅት እንዳልነበረ ገልጸው፤ በቅርቡ ሰባት የቆዳ ፋብሪካዎች በተደረገላቸው ድጋፍ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አግኝተዋል ነው ያሉት።
ይህም በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026