አዲስ አበባ፤ሰኔ 16/2017 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የገበያ ማዕከላት መስፋፋት ምርቶችን በበቂ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እያስቻላቸው መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው ሸማቾች ገለጹ።
በመዲናዋ የተገነቡ የገበያ ማዕከላት አምራቹንና ሸማቹን እንደ ድልድይ ሆኖ በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነቱን እና የዋጋ ንረትን በመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው፡፡
ለማሳያነትም ኢዜአ ከእነዚህ ማዕከላት አንዱ በሆነው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቁጥር ሁለት ሁለገብ የገበያ ማዕከልን እንቅስቃሴ ቅኝት አድርጓል።
ሸማቾች እንደሚሉትም በማዕከሉ በተመጣጣኝ ዋጋ የአትክልትና ፍራፍሬ እና የሰብል ምርቶችን እየገዙ እና እየተጠቀሙ መሆኑን አንስተዋል።
በማዕከሉ ስትገበያይ ያገኘናት ሸማች አበበች አሰፋ እንደገለጸችው ፤ በማዕከሉ ሁሉንም አይነት አትክልትና ፍራፍሬ በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸመተች መሆኑን በመግለጽ፤ በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት እንዳገኘች ትናገራለች፡፡
ሌላው ያነጋገርነው ሸማች ተማም ጀማል በበኩሉ፤ ለእኛ ለሸማቾች መንግስት በየአቅራቢያችን በገነባቸው ማዕከላት አትክልትና ፍራፍሬዎችና የሰብል ምርቶችን በአቅራቢያችን በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት መቻላችን እፎይታ ሰጥቶናል ነው ያለው፡፡
የማዕከሉ መኖር ውጪ ላይ ካለው ገበያ ሰፊ ልዩነት እንዳለውና አቅማችንን ባማከለ ዋጋ እየተገበያየን ነው ያለችው ደግሞ የምስራች አባይነህ ናት፡፡
በማዕከሉ ያነጋገርናቸው አምራቾች መካከል አቶ ተስፉ ወጂ እንዳሉት፤የገበያ ማእከላት መኖራቸው የግብይቱን ሰንሰለት በማሳጠር ምርቶቻቸውን ለተጠቃሚ ለማድረስ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሰብል ምርቶችን ጤፍ ከ10ሺህ ብር ጀምሮ፣ ሽንኩርት ከ35 ብር ጀምሮ በመሸጥ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየሸጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላው ያነጋገርናቸው አምራች አቶ ደረጄ ጋሪ በበኩላቸው ምርቶችን ውጭ ካለው ገበያ እስከ ሃያ ፐርሰንት ቅናሽ ለህብረተሰቡ እያቀረቡ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በላፍቶ ቁጥር ሁለት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ከማል ሃጂ ሰኢድ እንዳሉት ፤ የገበያ ማዕከሉ መገንባት ለሸማችና ለአምራቹ ግንኙነት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ፍስሀ ጥበቡ ቢሮው ገበያ ለማረጋጋት የቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ምርቶች እንዲገቡ እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025