አዲስ አበባ፤ሰኔ 16/2017 (ኢዜአ)፦በቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመጨመር በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓት ማስፋት ይገባል ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ።
በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የተዘጋጀውና ትኩረቱን ቱሪዝምና ቴክኖሎጂ ላይ ያደረገ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ በመርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምንጭ ተብለው ከተለዩ ዘርፎች መካከል ቱሪዝም አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶችና ባህላዊ እሴቶች ቢኖሯትም ከዘርፉ የሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እምብዛም ሆኖ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ የለውጡ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት፣ ነባሮችን የማደስና ዘርፉን የማዘመን ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ነው ያሉት።
በዚህም ትርጉም ያለው ለውጥ በማምጣት አበረታች ውጤት እንዲመዘገብ አስቻይ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።
ዘርፉ ከሚያስገኘው ጠቀሜታና ካለው እምቅ ሀብት አኳያ አሁንም ብዙ ስራዎች ያስፈልጋል ሲሉ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
በተለይም በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓት በማስፋት በቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መጨመር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
እንደሀገር እየተከናወነ ያለውን ቴክኖሎጂ መር የኢኮኖሚ ግንባታ ከዳር በማድረስ በኩል የቱሪዝም ዘርፉ ከዚህም በላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅበታል ብለዋል።
በፎረሙ ላይ ለእይታ የቀረቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለቱሪዝም ልማት ያላቸው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን ጠቁመው በዘርፉ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ያሳያሉ ነው ያሉት።
በመሆኑም በመንግስት ከሚከናወኑ ተግባራት በዘለለ ከግሉ ዘርፍና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከተሰማሩ አካላት ጋር በመተባበር እየተመዘገበ ያለውን ስኬት ማስቀጠል ያስፈልጋል ሲሉም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ በበኩላቸው በክልሉ ያሉ የቱሪዝም ሀብቶችን የማስተዋወቅ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
ዛሬ በይፋ የተጀመረውና ለሁለት ቀናት የሚካሔደው ይህ ፎረም የዚሁ አካል መሆኑን በማስረዳት።
ክልሉ ለቱሪዝም ልማት ምቹ የሆኑ ስፍራዎች በብዛት ያሉበት ከመሆኑ ባሻገር የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ባህላዊ እሴቶችና የአኗኗር ዘየዎች ያሉበት መሆኑ ደግሞ ለዘርፉ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
በመሆኑም የቱሪዝም ሃብቶችን የማስተዋወቅ ስራው በተገቢው መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው ለዚህም ዘመኑን የሚመጥን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።
ፎረሙ በዋናነት በዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ቴክኖሎጂዎች የሚተዋወቁበት፣ ተሞክሮ የሚቀሰምበትና ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያግዙ ውይይቶች የሚካሔዱበት መሆኑንም አብራርተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025