አምቦ፤ ሰኔ 19/2017 (ኢዜአ)፡-በምዕራብ ሸዋ ዞን የማር ልማት ኢኒሼቲቭን በመተግበርና የአርሶ አደሮችን ግንዛቤ በማሳደግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ማሳደግ መቻሉን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ተረፈ አራርሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ ባለፉት አሥር ወራት የተሻለ የማር ምርት ለማግኘት ታቅዶ ሲሰራ ቆይቷል።
ለእዚህም የማር ልማት ኢኒሼቲቭን ከመተግበር ባለፈ የአርሶ አደሮች ግንዛቤ በማሳደግ ምርታማነትና የልማቱን ተሳታፊዎች ተጠቃሚነት ለማሳደግ መቻሉን ነው የተናገሩት።
እንደ ሀላፊው ገለጻ አርሶ አደሮቹ ከባህላዊ ቀፎ ወደ ዘመናዊ ቆፎ ተሸጋግረው ውጤታማ እንዲሆኑ ግንዛቤያቸውን የማሳደግ ሥራ የተሰራ ሲሆን የንብ ቀፎ ድጋፍም ተደርጎላቸዋል።
በዚህም በቡድን ተደራጅተው በንብ ማነብ ሥራ ለተሰማሩ አርሶ አደሮችና ወጣቶች ከ46 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች መከፋፈሉን የጠቆሙት አቶ ተረፈ በዚህም አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።
በልማቱ ከ24 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችና ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን በዚህም ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
ከልማቱ ተሳታፊ አርሶ አደሮች መካከል የወልመራ ወረዳ አርሶ አደር አቶ ጌታቸው ደንደና እንዳሉት በተሰጣቸው 5 ዘመናዊ ቀፎዎች በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርተው ተጠቀሚ መሆን ችለዋል።
ልማቱን በማስፋፋት በዚህ ዓመት የቀፎዎቹን ቁጥር ወደ 22 ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል።
ከአንድ ባህላዊ ቀፎ እስከ 5 ኪሎ ግራም ማር ያገኙ የነበረው በአሁኑ ወቅት ከእያንዳንዱ ዘመናዊ ቀፎ 12 ኪሎ ግራም ማር ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል።
ዘንድሮ ከ22 ዘመናዊና አንድ ባህላዊ ቀፎዎች 269 ኪሎ ግራም ማር በማግኘታቸው ሥራውን ይበልጥ ለማስፋፋት እንዳነሳሳቸውም ነው የተናገሩት፡፡
ሌላው በአምቦ ወረዳ ጎሱ ቆራ ቀበሌ የሚኖሩት አቶ ወልደሰማያት ለታ በበኩላቸው የንብ ማነብ ስራን የሚያከናውኑት ከመደበኛ እርሻ ሥራ ጐን ለጐን በመሆኑ ከዘርፉ ባገኙት ገቢ ኑሯቸው እየተሻሻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ካሏቸው 38 ዘመናዊ፣ የሽግግርና ባህላዊ ቀፎዎች በዓመት ሁለት ጊዜ በማምረት ለገበያ ማቅረባቸውን ገልጸው በቀጣይ በስፋት ለማምረት እየተዘጋጁ መሆናቸው አንስተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025