
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2017(ኢዜአ)፦ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የቡና ቅምሻ ማዕከል መቋቋሙ ወደ ውጭ የሚላከው ቡና ጥራት እንዲሻሻልና የውጭ ድርጅቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ለኢዜአ እንደገለጹት የቡና ጥራትን ለማሻሻል የቡና ቅምሻ ማዕከላትን ማስፋፋት አስፈላጊ ነው።
በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የቡና ቅምሻ ማዕከል መቋቋሙ ወደ ውጭ የሚላከው ቡና ጥራት እንዲሻሻልና የውጭ ድርጅቶች በቡና ዘርፍ እንዲሰማሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለቡናው ዘርፍ የተሰጠው ልዩ ትኩረት፣ የቡና ስትራቴጂ መተግበሩና የመዋቅር አደረጃጀትና መመሪያዎችን የማሻሻል ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ እንዲመዘገብ ማስቻላቸውንም አክለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከስምንት ቢሊየን በላይ የቡና ችግኞች በመተከላቸው ምርታማነት እንዲሻሻልና ወደ ውጭ የሚላከው ቡና መጠን እንዲጨምር አድርጓል ነው ያሉት።
በዘርፉ የመጡ ለውጦች በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከቡና ወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ከሶስት እጥፍ በላይ እንዲያድግ አስችሏል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ 11 ወራት 280ሺህ 887 ቶን ቡና ወደ ውጭ ለመላክ ታቅዶ 409ሺህ 605 ቶን ቡና መላኩንና ከፍተኛ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
በቡና ዘርፍ የተደረገው ማሻሻያ ፍቃድ የተሰጠው አርሶ አደር ወደ ውጭ ቀጥታ እንዲልክ እድል መፍጠሩንና በዚህም ከ100 በላይ አርሶ አደሮች የቡና ምርታቸውን ቀጥታ ወደ ውጭ መላክ መጀመራቸውን አንስተዋል።
ይህም ጥራት ያለው ቡና ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ፣ የአርሶ አደሮችና የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ማስቻሉን ተናግረዋል።
አዲስ የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት በተነደፈው ስትራቴጂ መሰረት በተያዘው ዓመት ወደ አዳዲስ 20 ሀገራት መላክ መጀመሩንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡና ማህበር ፕሬዝዳንት ሁሴን አምቦ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ቡናን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀን ነው ብለዋል።
በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የቡና ቱሪዝምና ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑንም ለአብነት አንስተዋል።
ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣንና ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የሲዳማ ባለልዩ ጣዕም ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የተጀመረው ስራ በሌሎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የቡና ምርታማነት በምርምርና በእውቀት ለመደገፍ በቡና አብቃይ አካባቢዎች ካሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።
ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀዋሳ ከተማን በማልማት የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Jun 14, 2026
ጋምቤላ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ...
Jun 11, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማ...
Jun 4, 2026
ዲላ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ከ40 በላይ የንግድ ተቋማትና አጋር አካላት ተሳትፈውበት በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችን እና የኢ...
May 25, 2026