አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017 (ኢዜአ)፦ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም የፋይናንስ መዋቅር ለሁሉም የሚሰራ መሆን አለበት ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ።
አራተኛው ዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ፋይናንስ ኮንፍረንስ በስፔን ሲቪያ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
“የግሉን ዘርፍ የንግድ እና ፋይናንስ አቅሞች መጠቀም” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ውይይት ከኮንፍረንሱ ጎን ለጎን ተካሄዷል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ሙሉ የኢኮኖሚ አቅምን ለመጠቀም በዓለም የፋይናንስ ስርዓት ላይ አፋጣኝ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የግሉ ዘርፍ የንግድ እና ፋይናንስ ስራ ተደጋጋፊ ብቻ ሳይሆኑ ለሁሉን አቀፍ እድገት፣ ስራ እድል ፈጠራ እና ለአረንጓዴ ሽግግር ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ለአህጉሪቷ ትልቅ ለውጥ የፈጠረ ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ ለአነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚደረገውን ድጋፍ መጨመር፣ ዘላቂ ፋይናንስ ማበረታት እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመሳብ አቅም ማሳደግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
አፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ያለባት፣ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች እና እየተለወጠች ያለች አህጉር ናት ብለዋል።
የካፒታል አቅምን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የልማት አጀንዳዎች ጋር ማስተሳሰር ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ሊቀ መንበሩ ለዚህም 21ኛውን ክፍለ ዘመን የሚመጥን እና ለሁሉም የሚሰራ ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓት መገንባት እንደሚገባ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025