🔇Unmute
ሀዋሳ ፤ ጥቅምት 1/2018 (ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ለኢንዱስትሪ ግብአትና ገበያን ለማረጋጋት አቅም መፍጠራቸውን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
"ምርታማነትን ማሳደግ ለቤተሰብ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አመታዊ የሴክተር ጉባኤ በሃዋሳ እየተካሄደ ነው።
የቢሮው ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በሰብል ልማት፣ በበጋ መስኖና በቡና ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚሆኑና ገበያን ማረጋጋት የሚያስችል አቅም መፍጠራቸውን ገልጸዋል ።
በሂደቱም ከፍተኛ የስራ እድል መፈጠሩን የጠቀሱት ሃላፊው በ2016/17 የምርት ዘመን የመኸር ወቅት ከ106 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና ሰብሎች መልማቱን አስታውሰዋል።
በበልግ የለማውን 72 ሺህ ሄክታር ጨምሮ ከ319 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ የቀረበ ሲሆን በምርጥ ዘርና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ካለፉት አመታት የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ተናግረዋል።
የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ኢንዱስትሪዎችና ባለሃብቶችን በማሳተፍ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለቡና አብቃይ አካባቢዎች መድረሱን ገልጸዋል።
በዚህም የቡና ምርታማነት ማደጉን ጠቅሰው በተጠናቀቀው በጀት አመት 39 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማእከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ብለዋል።
በበጋ መስኖም በሚለማው መሬት ሽፋንና በምርታማነት ለውጥ የተመዘገበ ሲሆን የአትክልት ልማት ስራው ገበያን ማረጋጋት የሚያስችል አቅም የተፈጠረበት መሆኑን ገልጸዋል።
በቴክኖሎጂ፣ የውሃ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀምና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ የሚታዩ ውስንነቶችን ማረም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የቢሮው ሃላፊ አቶ መምሩ ገልጸዋል።
የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የገጠር ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዱሬሳ ሌዳሞ በበኩላቸው በዞኑ አርሶ አደሮችን በክላስተር በማደራጀት ከ26 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት እንደተቻለ ገልጸዋል።

በዚህም ከ75 ሺህ 400 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ከ7 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ማምረት መቻሉን ተናግረዋል።
በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የታየው ለውጥ የዝናብ መቆራረጥ ባጋጠማቸው አካባቢዎች የምርት እጥረት እንዳያጋጥም አስችሏል ያሉት ደግሞ የማእከላዊ ሲዳማ ዞን ገጠር ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ለጠፈ ላንቻ ናቸው።

በዘንድሮው የመስኖ ልማት ስራ ከ14 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ ገበያ ተኮር ምርቶች እንደሚመረቱ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ አስፋው ጎኖሶን ጨምሮ የመዋቅሩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሴክተሮች እውቅና ተሰጥቷል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026