የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የገጠር ኮሪደር ልማትን ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

Oct 14, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ጎንደር፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ):-የጎንደር ከተማ አስተዳደር በስሩ ባሉ ሁለት የገጠር ቀበሌዎች የገጠር ኮሪደር ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተናገሩ፡፡

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አቶ ቻላቸው ዳኘው ለኢዜአ እንደገለጹት የገጠር ኮሪደር ልማቱ የሚተገበረው በአዘዞ ተክለሃይማኖት እና ሳቢያ ሳይና በተባሉ ሁለት የገጠር ቀበሌዎች ነው።

በአሁኑ ወቅትም የኮሪደር ልማቱን የሚመሩ ኮሚቴዎችን ከማቋቋም ባለፈ ከሚተገበርባቸው ቀበሌዎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱን ለማስተግበር የሚያስችል ዕቅድ በማዘጋጀት በተያዘው በጀት ዓመት ሥራውን ለማከናወን እየተሰራ መሆኑንም አቶ ቻላቸው ተናግረዋል፡፡

በልማቱም ሞዴል የአርሶ አደር መኖሪያ ቤቶች፣ የመንገድ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃና በታዳሽ ሃይል ላይ የተመሰረቱ የኢነርጂ አማራጮች እንደሚተገበሩ ነው የገለጹት።

የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ በመቀየር ዘመናዊ አኗኗርን የሚያጎናጽፍና አዲስ የአስተሳሰብ እይታን የሚያሰፋ በመሆኑ ለሀገራዊ እድገት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።

በጎንደር ከተማ እየተገነባ ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ የከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025