የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ለአካል ጉዳተኝነት ሳንበገር መንግስት ባመቻቸልን የሥራ ዕድል ተጠቅመን ውጤታማ እየሆንን ነው

Oct 17, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ፣ ጥቅምት 6/2018 (ኢዜአ):-አካል ጉዳተኝነት ሳይበግራቸው መንግስት ባመቻቸላቸው የሥራ ዕድል በመጠቀም ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን በወላይታ ሶዶ ከተማ ተደራጅተው ወደሥራ የገቡ አካል ጉዳተኞች ገለጹ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ በክልሉ የአካል ጉዳተኞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ በርካቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጿል።


በወላይታ ሶዶ ከተማ የአማኑኤል አካል ጉዳተኞች ማህበር መስራች ወጣት ብርሃኑ ስምኦን እንደገለጸው አካል ጉዳተኛ ቢሆንም ሠርቶ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ግንዛቤ በመያዙ ተደራጅቶ ወደሥራ መግባቱን ተናግሯል።

ወደሥራ ለመግባት ካገኘው የህይወት ክህሎት ስልጥና በተጨማሪ በመንግስት የተመቻቸላቸውን የመነሻ ብድርና የመስሪያ ቦታ ድጋፍ በአግባቡ በመጠቀም ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግሯል።



ሥራቸውን ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ የሚሆን ክራንች በማምረት መጀመራቸውን ገልጾ፣ በሥራ ሂደት የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢገጥሙም ተቋቁመው እድገት እያስመዘገቡ መምጣታቸውን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ማህበሩ ለአካል ጉዳተኞች የሚሆኑ ዘመናዊ ክራንቾች፣ ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም የታካሚ አልጋዎችና ሌሎች ቁሶችን ጨምሮ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን በማምረት ለገበያ እንደሚያቀርብ ነው የተናገረው።

ከመንግስት ባገኙት 60 ሺህ ብር ብድር ሥራቸውን ቢጀምሩም በአሁኑ ወቅት ካፒታላቸውን ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ከማድረስ ባለፈ ለሌሎች ሰዎችም የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አመልክቷል።


የማህበሩ ገንዘብ ያዥ ወጣት በላይ ጤቻ በበኩሉ በማህበር ተደራጅተው ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ለራሳቸው ክራንች ለመግዛት እንኳ ይቸገሩ እንደነበር አስታውሷል።

ለአካል ጉዳተኝነት ሳይበገሩ ጠንክረው በመስራታቸው ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጾ፣ በዚህም ተጠቃሚነታቸው እያደገና ችግራቸውም እየተፈታ መምጣቱን ተናግሯል።

በማህበሩ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሆነው ወጣት ሰለሞን አበበ በበኩሉ በስራው ወርሃዊ ገቢ ከማግኘት በተጨማሪ በቂ ክህሎትና ሙያ እያገኘ መሆኑን ተናግሯል።


በክልሉ የአካል ጉዳተኞችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት በቅንጅት እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል እና የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ ናቸው።

በተለያዩ የሙያ መስኮች የክህሎት ስልጠና ወስደው በማህበር ሥራ የጀመሩ አካል ጉዳተኞችም ኑሯቸው እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።

አካል ጉዳተኝነት አለመቻል እንዳልሆነ በተግባር እያሳዩ መሆኑን ገልጸው፣ ውጤታማ ሥራ እያከናወኑ ካሉ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት መከካል የአማኑኤል አካል ጉዳተኞች የቤትና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ ማህበር አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።


እንደኃላፊው ገለጻ ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻዎች ጋር በመቀናጀት የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማስቀጠል እየሰራ ሲሆን በዚህም ከክህሎት ስልጠና በተጨማሪ የተለያዩ ድጋፎች ያደርጋል።

ባለፈው በጀት ዓመት በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ዘመናዊ ዊልቸሮች መሰራጨቱን ገልጸው፣ አካል ጉዳተኞቹ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች እንዲሳተፉ የማድረግ ስራ ይጠናከራል ብለዋል።

ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግም የመነሻ ብድር፣ የማምረቻ እና የመሸጫ ቦታ በማቅረብ ወደስራ ከማስገባት ባለፈ የገበያ ትስስር ለመፍጠር በቅንጅት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025