የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጥራትና ጊዜ እንዲጠናቀቁ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል

Oct 29, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያን ከበለጸጉ ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ መሰረት የሚጥሉ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጥራትና የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን አጠናቃ ባስመረቀችበት ማግስት የጉባ ብስራቶች የሆኑ የ30 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርጋለች፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ግንባታ፣ የኒውክሌር ሀይል ማበልጸጊያ፣ የጋዝ ማምረት፣ የነዳጅ ማጣሪያ እና በስድስት ዓመታት ውስጥ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ቤቶች ግንባታ ናቸው፡፡

ፕሮጀክቶቹ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት ለሕዝቡ የመልማት ፍላጎት ምላሽ የሚሰጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በመሰረታዊነት የሚቀይሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መብራቱ መለስ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ ትላልቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡


ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያፋጥኑ ወሳኝ ርምጃዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ሌላው የምክር ቤት አባል አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት ስሟ በድህነት ሲጠቀስ የነበረበትን የታሪክ ምዕራፍ የሚቋጩ እና በሌላ ገጽታ የሚያስተዋውቁ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡


ግንባታቸው የተጀመሩና በሂደት ላይ ያሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን ካደጉ ሀገራት ተርታ የሚያሰልፉ መሆናቸውን ገልጸው፤ የኢትዮጵያን በጎ ገጽታም ይገነባሉ ብለዋል፡፡

ሌላዋ የምክር ቤት አባል አዲሷ አሰፋ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለአፍሪካ ትሩፋት የሚሆኑ የልማት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጓን ገልጸዋል፡፡


ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፕሮጀክቶችን ገቢራዊነት ይከታተላል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025