🔇Unmute
ጋምቤላ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በተሰማሩ ባለሃብቶች ከ70 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቅባት ሰብሎች መልማቱን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት 2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ያስመዘገቡ 55 ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት ፈቃድ መውሰዳቸውንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሎው ኡቡፕ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉን የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች በማስተዋወቅ የዘርፉን ውጤታማነት ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
እየተከናወኑ ባሉት ስራዎችም ግብርናን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች በርካታ ባለሃብቶች ወደ ክልሉ ገብተው እያለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በግብርናው ዘርፍ እየተደረገ ባለው የድጋፍና ክትትል ስራ ከ300 በላይ ባለሃብቶች በሙሉ አቅማቸው ወደ ልማት መግባታቸውን ገልጸዋል።
አልሚዎቹ በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ70ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሰሊጥና የማሾ ሰብሎች ማልማታቸውን ተናግረዋል።
ተግባሩን በማጠናከር በበጀት ዓመቱ በክልሉ የተፈጠረውን አስተማማኝ ሰላምና ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም ከ360 የሚበልጡ ባለሃብቶችን በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንዲስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ለመቀበል ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቀዋል።
በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በክልሉ በተጠቀሱት ዘርፎች 2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ያስመዘገቡ 55 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
በግብርና ኢንቨስትመንት ከተሰማሩት ባለሃብቶች መካከል የፍቅርማሪያም አንዳርጌ እርሻ ልማት ስራ አስኪያጅ ፈንታሁን አራጋው በሰጡት አስተያየት በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ560 ሄክታር በላይ መሬት በማሾ ሰብል ማልታቸውን ተናግረዋል።
ከለማው መሬትም ከ5ሺህ 600 ኩንታል በላይ የማሾ ምርት እንደሚጠበቅ ጠቁመው ምርቱ ካለፈው ዓመት ጀምሮ የገበያ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱንም አክለዋል።
ክልሉ ለእርሻ ስራ ምቹ ስነ-ምህዳርና የተራዘመ የዝናብ ስርጭት ያለው በመሆኑ በአንድ ዓመት ሁለት ጊዜ የማልማት እድል ያለ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የዚሁ እርሻ ልማት ወኪል ካሳ አስረሴ ናቸው።
በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ የማሾ፣ የሰሊጥና የሱፍ ምርት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ገቢያ ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ ሌሎች ባለሃብቶችም ሰብሉን በስፋት እያለሙ መሆኑን ገልጸዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025