🔇Unmute
ወራቤ ፤ ጥቅምት 23/2018 (ኢዜአ):- በስልጤ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በቅመማ ቅመም ሰብሎች መልማቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለፀ፡፡
ኢትዮጵያ ከ50 በላይ የቅመማ ቅመም ዓይነቶችን ለማምረት የሚያስችል የእርሻ ስነ-ምህዳርን እንደታደለች መረጃዎች ያመለክታሉ።
የቅመማ ቅመም ምርቶች ከሚሰጡት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ሰፋፊ ማሳ የማይፈልጉና በአነስተኛ ስፍራዎች እንዲሁም ለእርሻ ተግባር በማይውል መሬት ላይ የመብቀል ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡
በተጨማሪም ምርቶቹ የሚበቅሉበት መሬት ለምነቱን ጠብቆ እንዲቆይ የማድረግ ባህሪም እንዳላቸውም የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ።

በስልጤ ዞንም በተያዘው ዓመት ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በቅመማ ቅመም ሰብሎች መልማቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አህመዲን ለኢዜአ እንደገለፁት፡ በዞኑ ከቅመማ ቅመም ምርት የሚገኝን ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ ነው፡፡

ዞኑ ከግብርና ልማት ስራው በተጨማሪ በቅመማ ቅመም ልማት ያለውን እምቅ አቅም በማስፋት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
አካባቢው በዋናነት የበርበሬ፣ የሮዝመሪና ኮሰረት ቅመማ ቅመም ሰብሎችን በስፋት ለማልማት የሚያስችል ስነ-ምህዳር ያለው መሆኑን ተናግረው ምርቶቹን የማስፋትና ገቢውን የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም በዘርፉ የሚሰማሩ ዜጎች የማሳ ሽፋን እየጨመረ መምጣቱን ያነሱት አቶ ሳዲቅ በተያዘው በጀት ዓመትም በዞኑ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በቅመማ ቅመም ሰብሎች መልማቱን ለአብነት አንስተዋል፡፡

የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ቀድራላ ዋበላ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምርምር ተቋሙ የግብርና ስራን በምርምርና በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ከምርምር፣ ከዘር ብዜትና ቴክኖሎጂን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ የውጪ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ የሚረዱ የሮዝመሪና የኑግ ምርቶችን የማስፋት ስራን በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዚህም አርሶ አደሩ ከሌሎች የግብርና ልማት ስራዎቹ ጋር በጥምር ማምረትና ተጠቃሚ መሆን የሚችልበትን ምህዳር የመፍጠር ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡
በስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮ ወረዳ ሽልማት ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር አባስ ሀጂዙቤር እንደገለፁት፤ ከሌሎች የግብርና ልማት ስራዎቻቸው ጎን ለጎን የሮዝመሪንና የኮሰረት ቅመሞችን በማልማት ላይ ይገኛሉ፡፡

የሚያመርቱትን ምርት ለአካባቢው አርሶ አደሮች ከማሰራጨት ጀምሮ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
የቅመማ ቅመም ምርት ሰፋፊ ማሳና ጉልበት የማይፈልግ ከሌሎች ስራዎች ጎን ለጎን የሚለማ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ አማራጭ ሆኖ መገኘቱን ጠቅሰው እርሳቸውን ጨምሮ የሌሎችም ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ነው የተናገሩት፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025