🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፡- የፋሲል አብያተ መንግሥት እድሳት ታሪክን ጠብቆ ለልጆቻችን የማስቀጠል ትጋት ማሳያ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ መገምገማቸውን እና የታደሠውን የፋሲል ግቢ መመረቃቸው ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሰጡት ማብራሪያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የፋሲል አብያተ መንግሥትን እንዳዩ መጠገን እንዳለበት መወሰናቸውን አውስተዋል።
ይህ ቁርጠኝነትም አንድም የአካባቢውን ብሎም የዓለም ሀብት የሆነውን ቅርስ መታደግ ማስቻሉን ገልጸዋል።
ለመጠገን በነበረው ሂደትም የውስጥና የውጭ ፈተናዎች አጋጥመው እንደነበር አንስተዋል።
ከውጭ ያጋጠመው ፈተና ‘ይህን ቅርስ አትንኩት፤ ከነካችሁት ይፈርሳል፤ እንዳለ ይቀመጥ’ የሚል ትልቅ ተጽዕኖ እንደነበር ጠቁመው፤ የውጭውን ተጽዕኖ በማየትና ‘ጥገናው በሀገር ውስጥ አይቻልም’ የሚሉ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች ደግሞ ከውስጥ መነሳታቸውን ተናግረዋል።
እነዚህን ሁሉ ጫናዎች በመስበር ቅርሱ እንደገና ተወልዶ አሁን ለአገልግሎት መብቃቱን አስገንዝበው፤ ከዚህ አንጻር የፋሲል አብያተ መንግሥት ተጠገነ ከሚባል እንደገና ተወለደ ቢባል በይበልጥ ይገልጸዋል ብለዋል።
ይህም ኢትዮጵያ እንደምትችል ያሳል፤ ሌሎች ቅርሶችን ለመጠገን የሚያስችል ዐቅም በሀገር ውስጥ እንዳለንም ይመሠክራል ነው ሉት።
እድሳቱ በሀገር ውስጥ ተቋራጭ በስኬት መከናወኑን ጠቅሰው፤ በለውጡ መንግሥት ትላልቅ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች ዐቅም እያደገ መምጣቱን አመላክተዋል።
የፋሲል አብያተ መንግሥት ኢትዮጵያ ታላቅ እንደነበረች፣ አሁንም እንደሆነችና ወደፊትም እንደምትሆን የሚያሳይ ምልክታችን ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከመገጭ ግድብ ጋር በተያያዘ ከተጀመረ ረዥም ዓመታት መውሰዱን ጠቅሰው፤ የአካባቢውን መሬት ከማልማት ባለፈ ለጎንደር ከተማ የመጠጥ ውኃ እጥረት መፍትሔ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች በመዘግየቱ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት እንደነበር ጠቅሰው፤ እንደ አዲስ እየተሠራ ያለ ትልቅ ግድብ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም በሀገር ውስጥ ተቋራጭ በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ መሆኑን በመጠቆም፤ በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026