🔇Unmute
ባህር ዳር፤ ሕዳር 1/2018(ኢዜአ)፡-በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን ጽዳትና ውበት ይበልጥ ከማሳደጉ ባለፈ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት መስህብነቷ እንዲጨምር ማስቻሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
የአስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንዳለ ጋሻው እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ለከተማዋ እድገት ዘርፈ ብዙ ዕድል ይዞ መጥቷል።
ባህር ዳር በተፈጥሮ ውብ ከተማ ብትሆንም በኮሪደር ልማቱ ያላትን ውበት ይበልጥ ከፍ ያደረጉ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
እንደ አቶ ወንዳለ ገለጻ የከተማዋን ነዋሪዎችና ባለሀብቱን በማስተባበር 22 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ሥራ ለማከናወን ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል።
እስካሁን በተደረገ ጥረትም በመጀመሪያው ምዕራፍ በከተማው ከአጂፕ እስከ ቀድሞው ጊዮን ሆቴል 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ሥራ በማከናወን ለማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ከአልማ እስከ ዋተር ፍሮንት ደረጃውን የጠበቀ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን አፈጻጸሙም በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጹት።
ለመጀመሪያውና ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ጠቁመው፣ ለልማት ሥራው ማህበረሰቡ በተለያየ መንገድ እያደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በሦስተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ ከጣና ማሪና እስከ ዘጌ መገንጠያ ድረስ 4 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የልማት ሥራ እንደሚከናወንና በአሁኑ ወቅትም ልማቱ የሚነካቸው አካባቢዎችን ከሦስተኛ ወገን የማፅዳት ሥራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
የልማት ሥራውን በፍጥነት ለማከናወን የሥራ ተቋራጭና አማካሪ ድርጅቶችን የመለየት ሥራ መከናወኑንም አቶ ወንዳለ ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማቱ የመኪና እና የእግረኛ መንገድ፣ የአረንጓዴና የመዝናኛ ስፍራ እንዲሁም የብስክሌት መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን አካቶ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የኮሪደር ልማቱ ባህር ዳር ከተማን ይበልጥ ውብ፣ ፅዱና ማራኪ እያደረጋት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የቱሪስት መስህብነቷን ከመጨመር ባለፈ ለኢንቨስትመንትና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዳደረጋት አመልክተዋል።
የኮሪደር ልማቱ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በመጨረስ፣ የሥራ ባህልን በመቀየር እና የተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር መልካም ተሞክሮ የተገኘበት ነው ሲሉም አቶ ወንዳለ ገልጸዋል።
ማህበረሰቡ ለልማቱ በገንዘብ፣ በእውቀትና በተለያየ መንገድ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አቶ ወንዳለ ጠይቀዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025