የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

አርሶ አደሮች በሻይ ልማት ስራ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን እየሰሩ ነው

Nov 20, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ ፤ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፡- በማህበር ተደራጅተው በጀመሩት የሻይ ልማት ስራ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን እየሰሩ መሆኑን የኢሉአባቦር ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።

የዛሬ ሶስት ዓመት በማህበር ተደራጅተው የተከሉት ሻይ ደርሶ ለፋብሪካ ማቅረብ መጀመራቸውንም አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።

ከአርሶ አደሮቹ መካከል አቶ ታዬ ገብሬ እንዳሉት፤ ስራው በአጭር ጊዜ ለውጤት ይበቃል የሚል እምነት እንዳልነበራቸው አንስተው አሁን ለዚህ ደረጃ በቅቶ በማየታቸው ተነሳሽነታቸው ጨምሯል።


ዛሬ ላይ ለለቀማ ደርሶ ምርቱን በአካባቢያቸው ለሚገኘው ጉመሮ ሻይ ፋብሪካ ማስረከብ በመጀመራቸው ስራውን የበለጠ በማስፋት ተጠቃሚ ለመሆን መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

አርሶ አደር ከድር ጀማል በበኩላቸው የሻይ ልማት ስራቸው ውጤታማ በመሆኑ በቀጣይ በልዩ ትኩረት ስራውን ለማስፋፋት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል።


የግብርና ባለሙያዎች በሻይ ልማት ላይ ከቅድመ ዝግጅቱ ጀምሮ በችግኝ እና በማዳበሪያ አቅርቦት ሲያግዟቸው እንደነበረም አስታውሰዋል።

አቶ ምትኩ አስፋው እና አቶ ፍራኦል ጫንያለው የተባሉ አርሶ አደሮችም እንዲሁ ለሻይ ልማቱ አስፈላጊውን እንክብካቤ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸው በጽናት የሚሰራ ስራ ሁሌም ውጤት እንደሚኖረው አይተንበታል ብለዋል።


አሁን ላይ የደረሰውን የሻይ ቅጠል ከጉመሮ ሻይ ፋብሪካ ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ማስረከብ በመጀመራቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

የጉማሮ ሻይ ቅጠል ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ምትኩ በበኩላቸው ፋብሪካው የሻይ ቅጠሉን የሚረከበው አስፈላጊውን የማጓጓዣ አቅርቦት እና ባለሙያ በመመደብ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዋጋ ጋር በተያያዘ የማምረቻ ወጪያቸውንና በገበያ ላይ ያለውን ተለዋዋጭና ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በየዓመቱ በሚታደስ ውል ምርቱን የሚቀበሉ መሆናቸውንም አንስተዋል።

በዚህም አርሶ አደሩና ድርጅቱ በጋራ ተጠቃሚ በሚሆኑበት ሁኔታ ላይ በዘላቂነት እንደሚሰራ ገልጸዋል።


በኢሉባቦር ዞን ባለፉት ዓመታት ለሻይ ልማት ስራ በተሰጠው ትኩረት በስምንት ወረዳዎች የልማት ስራው መጀመሩን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቻላቸው አዱኛ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በዞኑ ከ1 ሺህ 600 ሔክታር በላይ መሬት በሻይ እየለማ መሆኑን ገልጸው ከዚህም ውስጥ 573 ሔክታር ያህሉ በአርሶ አደሮች የለማ ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በኩታ ገጠም ከለማው ሻይም በ300 ሔክታር መሬት ላይ በሶስት ማህበራት የተተከለው ሻይ ለለቀማ በመድረሱ ከጉመሮ ሻይ ፋብሪካ ጋር የገበያ ትስስር ተፈጥሮ ወደ ለቀማ መገባቱንም አስታውሰዋል።

በቀጣይም የሻይ ልማት ስራውን ከማስፋፋት ጎን ለጎን ማህበራቱ የሻይ ቅጠል ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እንዲኖራቸው የማድረግ ስራ እንደሚሰራም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025