የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል

Nov 20, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፡-በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ ባለሃብቶችን ለመሳብና የንግድ ትስስሩን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ገለፁ።

በተለያዩ አገራት ያሉ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ለኢዜአ እንዳሉት የኢትዮጵያን ምርቶች በማስተዋወቅ በአለም ገበያ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሰኢድ መሀመድ(ዶ/ር) ፤ኩዌት የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አጋርና በስራ ስምሪት መዳረሻ ከሆኑ አገራት አንዷ መሆኗን ተናግረዋል።


የኢትዮጵያን የስጋ፣ ቡና፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በኩዌት ገበያ የማስተዋወቅ ስራዎች መጀመራቸውን ገልፀው በቀጣይ በርካታ የኢትዮጵያ ምርቶች በኩዌት ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚረዱ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

ምርቶቹን በኩዌት ገበያ በስፋት ለማስተዋወቅና የሁለቱ አገራት ንግድ ምክር ቤቶች አስፈላጊ ስራዎችን በጋራ እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የኩዌት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚረዱ ተግባራት መጀመራቸውን አስታውቀው የአገራቱን የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ።

አሁን ላይ 22 የኩዌት ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መሰማራታቸውን አንስተው ስትራቴጂክ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ለማድረግ ድርድሮች መጀመራቸውን ነው የገለፁት።

በእንግሊዝ እና ሰሜን አየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን፤ በኤምባሲው የቢዝነስ ማስተዋወቂያ ፎረሞችን በማዘጋጀትና መድረኮችን በመጠቀም ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።


ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንም በተለዩ የትኩረት መስኮች እንዲሰማሩ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ በአካባቢዎቹ ያለው የቢዝነስ ኮሙዩኒቲ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አይተናል ብለዋል።

በቅርቡ የኢትዮጵያና የታላቋ ብሪታንያ የንግድ ምክር ቤት መቋቋሙንና የመጀመሪያ የማስተዋወቂያ መድረክ በለንደን መካሄዱን አንስተዋል።

በቀጣይም የቢዝነስ ልዑክ ቡደኑ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የማስተዋወቂያ ፎረም እንደሚካሄድ ነው የጠቆሙት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025