የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የአፍሪካ የልማት መሰረትና የሰላም ማስከበር አውራ - ኢትዮጵያ

Sep 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስከብራ የኖረች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር፣ ለአህጉሩ ሀገራት የነፃነት፣ የልማትና የሰላም ማስከበር ጥረቶች ታሪካዊና መዋቅራዊ መሰረት በመጣል ግንባር ቀደም ሚና ስትጫወት ቆይታለች። ሀገሪቱ ለአፍሪካ አንድነት፣ ለቀጣናዊ ትስስርና ለሰላም ማስከበር ያበረከተችው አስተዋጽኦም የላቀ ነው።

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ገቢር ነበብ ሆኖ፣ ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጋራ ልማትና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የሚመራ ነው። አገሪቱ በአፍሪካ አህጉር በሚከናወኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የመሠረተ ልማት ትስስር፣ የሰላም ማስከበርና ተዛማጅ ሁለንተናዊ መስኮች የምትጫወተው የፊት አውራነትና የመሪነት ሚና በተጠናከረ ሁነታ ቀጥሏል።

የኢነርጂ እጥረት የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛ ማነቆ መሆኑን የተረዳችው ኢትዮጵያ፣ ግዙፍ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመገንባትና ጥቅም ላይ በማዋል አህጉራዊ አርአያነቷን እያስመሰከረች ትገኛለች። በዚህ ረገድ የላቀ ምሳሌ የሚሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ ለጎረቤት አገራትም አስተማማኝ የኃይል ምንጭ በመሆን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በጥብቅ መሠረት ላይ ጥሏል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የቀጣናውን የኢነርጂ ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ፣ ዘላቂ የኃይል ልማት ትስስርን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። በተጨማሪም ከታንዛኒያ፣ ከሩዋንዳ፣ እንዲሁም ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር የኃይል መስመሮችን ለመዘርጋትና ትስስሩን የበለጠ ለማስፋፋት በትጋት እየሰራች ትገኛለች።

የኢትዮጵያ የኃይል ልማት ፖሊሲ ያጋራ ተጠቃሚነትንና አብሮ ማደግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ጎረቤት አገራት የታዳሽ ሃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የድርሻዋን ማበርከቷን ቀጥላለች።

ኢትዮጵያ የቀጣናው የሎጅስቲክስና የትራንስፖርት ዋና ማዕከል በመሆንም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስርን እያጠናከረች ትገኛለች። የሀገሪቱ ተቋማዊ አምባሳደር የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አፍሪካን ከእስያ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ጋር በማያያዝ ረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወት ወሳኝ የትራንስፖርት አውታር ሆኗል። በተጨማሪም ከጂቡቲ፣ ኬንያ እና ሱዳን ጋር የተዘረጉት የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ መሰረተ ልማቶች፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿና ከቀጣናው አገራት ጋር ያላትን የንግድና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በጥራትና በፍጥነት ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማትም ከሀገራዊና ቀጣናዊ ወሰኖች የተሻገረ ግብ በመሰነቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም እና የተፈጥሮ ሀብትን ለመታደግ ያለመ ግዙፍ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ታላቅ የልማት ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነትንና የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) ከማሳካት አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅናና አድናቆት ተችሮታል።

የአባይ ወንዝ መነሻ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሯ አማካኝነት የታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት በጎርፍና በደለል እንዳይጠቁ ከመጠበቋም በላይ፣ የጋራ የውሃ ሀብትን በዘላቂነት ለመንከባከብና ለመጠበቅ በትጋት እየሠራች ትገኛለች። ይህ ጥረት የወንዙን ዓመታዊ የውሃ ፍሰት በመጠበቅና የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ ለቀጣናው አገራት ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ነው።

ኢትዮጵያ በቀጣናዊና አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ስማሪዎች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ አሁንም በግንባር ቀደምትነት እየሠራች ትገኛለች። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር በሶማሊያ (AMISOM/ATMIS)፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኮንጎና በሌሎችም የአህጉሪቱ የግጭት ቀጣናዎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን በማሰማራት ረገድ የኢትዮጵያን ያህል ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለና አስተዋጽኦ ያደረገ አገር የለም ለማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያ በተለይም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አል-ሸባብን የመሳሰሉ አክራሪና ሽብርተኛ ቡድኖች ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ሽብርተኝነትን በግንባር ቀደምትነት እየታገለች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሶማሊያ መንግሥት ተቋማት እንዲጠናከሩና ቀጣናው ሙሉ በሙሉ ከሽብር ስጋት ነፃ እንዲሆን በጀግንነት፣ በውጤታማነትና በላቀ ቁርጠኝነት የተጣለባቸውን አገራዊና አህጉራዊ ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ።

የአፍሪካን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ስምምነት በማጽደቅና በተግባር ላይ በማዋል ረገድም ኢትዮጵያ የጎላ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። አህጉራዊ የንግድ ውሎችና ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የጉምሩክ አሠራሮች የተቀላጠፉና ዘመናዊ እንዲሆኑ በትጋት እየሠራች ነው።

ለፓን-አፍሪካኒዝም እሴቶች መጠናከር፣ ለአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ነፃነትና ሉዓላዊነት መረጋገጥ የኢትዮጵያ የታሪክና የፖሊሲ ካፒታል ጠንካራ መሠረት ሆኗል። በአጠቃላይ፣ አገሪቱ የአፍሪካ የልማት ምሰሶና የሰላም ማስከበር ግንባር ቀደም መሪ በመሆን ታሪካዊና አህጉራዊ ኃላፊነቷን በተጠናከረ ሁኔታ እየተወጣች ትገኛለች።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቱን እውነተኛ ትረካዎችና የመረጃ ልውውጥ በግንባር ቀደምትነት የምታስተጋባ "የአፍሪካ ድምፅ" ስትሆን፣ እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባሉ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶቿና ለጎረቤት ሀገራት በምታቀርበው ንጹህ ኤሌክትሪክ የቀጣናውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ትደግፋለች።

በተጨማሪም በባቡር፣ በአውራ ጎዳናዎች፣ በቴሌኮም፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢጋድ (IGAD) በኩል አህጉራዊ የመሰረተ ልማትና የንግድ ትስስርን በማጠናከር፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነትን ከመደገፍ ባሻገር በሰላም ማስከበርና በቀጣናዊ ድርድሮች ረገድ የምትጫወተው ሚና ለዘላቂ ልማትና ሰላም ትልቅ ዋስትና ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026