የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት የዜጎችን የስራ ባህል እየቀየረ ነው

Sep 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፣ መስከረም 11/2019 (ኢዜአ)፦ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት የዜጎችን የሥራ ባህል በመቀየር ከተረጂነት ወደ አምራችነት እያሸጋገረ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው።


በሚኒስቴሩ የከተሞች ምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተሾመ እንደተናገሩት በከተሞች እየተተገበረ ያለው የልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት ዜጎች አምራች እንዲሆኑ እያደረገ ነው።

በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ በ88 ከተሞች እየተተገበረ ያለው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ በከተሞች ላይ በአረንጓዴ አሻራ፣ በጽዳትና ውበት፣ በአረንጓዴ ልማት አፈጻጸም ውጤታማ ስራ እያከናወነ መሆኑን የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ተናግረዋል።

በያዝነው ዓመትም ለሶስተኛ ጊዜ ከ250 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ፋይናንስ ከአለም ባንክ እንደተመደበ ገልጸው ከሚቀጥለው ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

ዘንድሮ በሚከናወነው ፕሮጀክት ከ420 ሺ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ የሚከናወን ሲሆን የአካባቢ ልማት፣ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ አና ጎዳና ላይ የወጡ ዜጎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ስራ ትኩረት የሚሰጠው ነው ብለዋል።


የሲዳማ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ብሩክ ሰለሞን በበኩላቸው፤ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በዘላቂነት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት እያሸጋገረ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮግራሙ በክልሉ ሀዋሳና ይርጋለም ከተሞች ተግባራዊ መደረጉን ገልጸው በአረንጓዴ ልማት፣ በከተሞች ውበትና ጽዳት ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል።

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ ፕሮጀክት በከተሞች የሚከናወኑ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ውጤታማነት እያረጋገጡ ነው ያሉት ደግሞ የሃዋሳ ከተማ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ ናቸው።


ባለፉት አመታት በሀዋሳ ከተማ ተግባራዊ የተደረገው ይኸው ፕሮግራም በርካታ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ማሸጋገሩን ገልፀዋል።

ሃዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማእከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች እንደሚጠናከሩ የገለጹት ኃላፊው የመደመር መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የከተሞችን ትንሳኤ እያረጋገጠ መሆኑን አስረድተዋል።

በመድረኩ ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በሃዋሳ ከተማ በልማታዊ ሴፍቲኔት የተከናወኑ ስራዎችንና የኮሪደር ልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026