የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በድሬዳዋ አስተዳደር የተካሔዱ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አስችለዋል

Sep 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መስከረም 16/2018(ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሔዱ ያሉ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያስቻሉ ናቸው ሲሉ ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ።

ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልም 12 ቢሊዮን ብር በጀት መመደቡም ተገልጿል።

ካለፉት አምስት አመታት ጀምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር በገጠርና በከተማ ከ22 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የልማት ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በመደረግ ላይ ናቸው።

በተለይ በመደመር መንግስት በከተማ እና በገጠር ተግባራዊ የተደረጉ ፕሮጀክቶች የነዋሪውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደጋቸው በላቀ ደረጃ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የተናገሩት።


በተጠናቀቀው ሳምንትም ለትራፊክ ክፍት የሆነውን የ 4 ነጥብ 2 ኪሎሜትር የኮንክሪት አስፋልት መንገድ የዚሁ አካል መሆኑም አንስተዋል።

ከንቲባ ከድር ጁሃር በመንገዱ ምረቃ ወቅት እንደተናገሩት በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፉት አምስት አመታት የተተገበሩት ፕሮጀክቶች ድሬዳዋን ውብና ተመራጭ የስራ እና የመኖሪያ ማዕከል አድርጓታል።


የድሬደዋ አስተዳደር የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽነር ኃይለማሪያም ዳዲ በበኩላቸው ፤ በዘንድሮ በጀት አመት የነዋሪዎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት 12 ቢሊዮን ብር ተመድቧል።

በዚህም 146 አዳዲስና ነባር ፕሮጀክቶች በመተግበር ላይ ናቸው ነው ያሉት።

ባለፉት አምስት አመታት 31 ግዙፍ የመንገድ፣ የንፁህ መጠጥ እና የመስኖ ፕሮጀክቶች ፣ የገበያ ማዕከላት እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች መገንባታቸውን ነው የተናገሩት።

በዚህም የነዋሪዎችን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት መቻሉን ነው ያስታወቁት።

አስተዳደሩ በተያዘው በጀት ዓመት የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመስኖ ፣ የአስፋልት መንገዶች፣ የኮሪደር ልማት ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት በማስፋት የመንግስት አገልግሎት የማዘመን ስራ ትኩረት የተሰጠባቸው ስራዎች ናቸው ብለዋል።

የኮሪደር ልማትን በማስቀጠልና የከተማ ነዋሪዎችን የመጠጥ ውሃ ችግር በማቃለል የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ ለመፍታት ጥረቱ መቀጠሉን ተናግረዋል።

በመከናወን ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የሚያሳድጉ ከመሆናቸው በተጨማሪ ድሬዳዋን የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ማዕከልነት ይበልጥ ያሳድጋሉ ብለዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026