🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦የቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር የዘርፉን ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ ገለጹ።
ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ውጤታማነት የሚያረጋግጡ የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ማሻሻያዎችን በማድረግና ታላላቅ እርምጃዎችን በመውሰድ እንዲሁም ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ጭምር ተግባራዊ አድርጋለች።
ይህ እርምጃ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ሰንቃ ሁለንተናዊ ዕድገቷን ለማስቀጠል ለምትጓዝ ሀገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ የተመራ የዘርፉ አመራሮችን ያካተተ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው የቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሥራ ጉብኝት አድርጓል።
በጉብኝቱ ወቅት በቲ.ኬ ቢዝነስ ግሩፕ (TK Business Group)፣ ፒ.ቲ. ኢንዶ ሱልጣን ጃያ (PT. Indo Sultan Jaya) እና ኦሊቨር ኦይል ሊሚትድ (Oliver Oil Limited) መካከል የጋራ የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራርመዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የተቀናጁ የግብርና-ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ልማት ለመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር እንደ አስፈላጊ መሣሪያ እየተጠቀመችበት ትገኛለች።

የዚህ እርምጃ ዋና ዓላማም የግብርና ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ከመላክ ይልቅ በሀገር ውስጥ እሴት ጨምሮ ማቀነባበርና ማምረት መሆኑን አስረድተዋል።
ይህም በአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፉ የማቀነባበር አቅምን ከማሳደግ ባለፈ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግርን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችን ማሳደግንና የኢትዮጵያ ምርቶችን በቀጣናዊና ዓለም አቀፍ የእሴት ሰንሰለት ማቀላቀልን ያጠናክራል ብለዋል።
የዛሬው የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነትም የኢትዮጵያን የግብርና እምቅ አቅም ወደ ኢንዱስትሪያዊ እሴት ለመቀየር የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም ከኢንዶኔዥያ እና ፓኪስታን የመጡ ኩባንያዎችና ኢንቨስተሮች ካፒታል ብቻ ሳይሆን ዕውቀት፣ ቴክኖሎጂ፣ የገበያ አቅምና የምርት ልምድ ይዘው በመምጣታቸው አጋርነቱ በኢትዮጵያ የአግሮ ኢንዱስትሪና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ ያለውን ዕድል ለማስፋት ያግዛል ነው ያሉት።
ስምምነቱ በግብርና ምርቶች ላይ እሴት መጨመር፣ ዘመናዊ ማቀነባበርና ማኑፋክቸሪንግ፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችን ማልማትና የኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር ላይ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት የገቢ ንግድ ጫናን ለመቀነስና የወጪ ንግድ ምርቶችን ለማሳደግ እንዲሁም የኢትዮጵያ አምራቾችን ወደ ቀጣናዊና ዓለም-አቀፍ የእሴት ሰንሰለት ለማቀላቀል ስምምነቱ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
አክለውም የአግሮ ኢንዱስትሪ ልማት የሚሳካው መንግሥት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና የግሉ ዘርፍ በጋራ በመሥራት ምቹ የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ፣ ቀልጣፋ አሠራርና የገበያ ትስስር ሲፈጠር መሆኑን ገልጸዋል።
በቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ አርሶ አደሮች፣ አቀናባሪዎች፣ አምራቾች፣ የሎጂስቲክስና የፋይናንስ አቅራቢዎች፣ የቴክኖሎጂ ተቋማትና ገበያዎችን በአንድ የኢንዱስትሪ ሥነ-ምህዳር ለማስተሳሰር መታቀዱን አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ ለምርታማ ኢንቨስትመንት፣ ለአጋርነትና ለረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪ ትብብር ክፍት መሆኗንም ጨምረው አስታውቀዋል።
ኢንቨስትመንቶቹ በሀገር ውስጥ የሠራተኞች ክህሎትን ማሳደግ፣ የአቅራቢዎችን አቅም ማጠናከር፣ ለአርሶ አደሮች የተሻለ ገበያ መፍጠርና የኢትዮጵያን ምርቶች ወደ ውጭ ገበያ ማስፋት የሚችሉ የጋራ እሴት እንዲፈጥሩ እንደሚፈለግ ገልጸዋል።
የቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከግብርና ምርት ማቀነባበር ባሻገር የአርሶ አደሮችን ከገበያ፣ ኢንቨስተሮችን ከጥሬ ዕቃ አቅርቦትና አምራቾችን ከቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ገበያ ጋር በማስተሳሰር የኢትዮጵያን የአግሮ ኢንዱስትሪ ሽግግር ለማፋጠን የሚጠበቅበት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰናይት መብሬ በበኩላቸው፣ የቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርና ጥሬ ዕቃን ወደ እሴት የተጨመረበት ምርት መቀየር የሚያስችሉ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ያካተተና ለኢንቨስትመንት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በፓርኩ የተፈረመው የጋራ የኢንቨስትመንት ስምምነትም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ባለሀብቶችን በማጣመር በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ለመጨመር፣ የማቀነባበርና የማምረት አቅምን ለማሳደግ እንዲሁም የአምራቾችን የገበያ ትስስር ለማጠናከር ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
ስምምነቱ የግሉን ዘርፍ በፓርኩ የሚያሳትፍ ሲሆን፣ የግብርና ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎችን፣ አቀናባሪዎችንና አምራቾችን በማስተሳሰር የግብርና ምርቶች የእሴት ሰንሰለትን ለማጠናከርና ተጨማሪ የሥራና የገበያ ዕድሎችን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...
Sep 15, 2026
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026