🔇Unmute
አሶሳ፤ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ከተረጂነት ለመላቀቅ የተያዘውን ዕቅድ የሚያሳኩ ናቸውሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተረጂነት ቅነሳና በምግብ ሉዓላዊነት ዙሪያ በተዘጋጀ የ5 ወራት ዕቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ወቅትም እንደተናገሩት፤ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ከተረጂነት ለመላቀቅ የተያዘውን ዕቅድ የሚያሳኩ ናቸው።
በክልሉ በቅርብ ዓመታት የተጀመረው ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን ትግበራ አበረታች ውጤት የታየበትና የስራ ባህልን የቀየረ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በቂ ምርትን በመያዝ አደጋን የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሐመድ አብዱላዚዝ በበኩላቸው፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመሸፈን በሚደረገው ጥረት በግብርናው ዘርፍ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
በዚህም በክልሉ የተለያዩ የግብርና ውጤቶችን በማምረት ለአደጋ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም አክለዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026