የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በከተማው የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ለውጦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላችንን እንወጣለን

Jun 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ዲላ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ በከተማው የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ለውጦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላችንን እንወጣለንሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መሰረት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የምክር ቤት ወንበር በማግኘት መንግሥት ለመመስረት የሚያስችለውን ድምጽ አግኝቷል።

ለኢዜአ አስተያየታቸው የሰጡ የዲላ ከተማ ነዋሪዎች በለውጡ መንግሥት በከተማው የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ለውጦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል መምህር ዮናስ ታደለ እንደተናገሩት፤ በከተሞች መሰረተ ልማትና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል።

እንዲሁም ህብረተሰቡን በማስተባበር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተደረጉ ጥረቶች ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት የሚደረገውን ጉዞ የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በከተማው የተመዘገበው ዘርፈ ብዙ ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በምርጫ ያሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ ከሚመሰርተው መንግሥት ጎን በመሰለፍ የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ነጻ፣ ገለልተኛና አሳታፊ በሆነ ምርጫ አሸናፊው ፓርቲ መታወቁ የዲሞክራሲ ባህል እየጎለበተ መምጣቱን የሚያመላክት መሆኑን ያነሱት ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ተስፋነሽ ኢሳያስ ናቸው።

በተለይ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

በከተማው የታየው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከአሸናፊ ፓርቲው ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር መምህርና ተመራማሪ ሰረቀብርሃን ለገሰ በበኩላቸው፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከዝግጅት እስከ ውጤት ገለልተኝነትና አሳታፊነት በተጨባጭ የተረጋገጠበት ነው ብለዋል።

በዴሞክራሲያዊ መንገድ ወደ ስልጣን የመጣ መንግሥት ለህዝብ የልማት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት አንጻር የተሻለ መሆኑን አንስተው አዲሱ መንግሥት የልማት ውጥኑን ከዳር እንዲያደርስ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026