የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ቢሮው ተግባራዊ ያደረጋቸው በቴክኖሎጂ የተደገፉ አዳዲስ አሠራሮች የአገልግሎት አሰጣጡን ከማዘመን ባለፈ የከተማዋን የገቢ አቅም አሳድጓል

Jun 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ተግባራዊ ያደረጋቸው በቴክኖሎጂ የተደገፉ አዳዲስ አሠራሮች የአገልግሎት አሰጣጡን ከማዘመን ባለፈ የከተማዋን የገቢ አቅም ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ቀደም ሲል ግብር ከፋዮች በአካል በመቅረብና የወረቀት ሰነዶችን በመያዝ ያገኙት የነበረውን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደ ኦንላይን ሥርዓት ማሸጋገር ችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሃመድ አብዱረህማን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ቢሮው ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ የሪፎርም ሥራዎችን አከናውኗል።

ግብር ከፋዮች በአካል ሳይመጡ በኢሜል እና በተዘረጋው የኦንላይን ሊንክ አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ከፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት የተቀናጀ የልማት ሥርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመዋል።

ይህ አዲስ አሠራር ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበት ምኅዳር የፈጠረ ሲሆን፣ የባለቤትነት ስም ዝውውርን ጨምሮ የተለያዩ የሕግ ተገዥነት አገልግሎቶችን ያካተተ መሆኑን አስረድተዋል።

ቢሮው በራሱ አቅም ያለማውን የዕዳ ክትትል ሥርዓት ወደ ተግባር በማስገባቱ በ17ቱም ቅርንጫፎች የሚወሰኑ የዕዳ ውሳኔዎችን በቅርበት ለመከታተልና የሚሰበሰበውን ገቢ ወደ ገንዘብ በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል።

የክሊራንስ አሰጣጥ ሂደቱን ይበልጥ ግልጽ፣ ቀልጣፋና እምነት የሚጣልበት ለማድረግ ባርኮድ ያለው አዲስ የኦንላይን አሠራር ተግባራዊ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

የተዘረጉት የዲጂታል አገልግሎቶች ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው ግብራቸውን እንዲያሳውቁና እንዲከፍሉ በማድረጉ፣ በየወሩ መጨረሻ ላይ በቅርንጫፍ ቢሮዎች ይታይ የነበረውን ከፍተኛ መጨናነቅና የረጅም ጊዜ ጥበቃ ማስቀረት መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

ቢሮው በቀጣዩ በጀት ዓመትም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮችን የሚያስተናግደውን የኢቲ ታክስ (eTax) ሥርዓት ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል በማሸጋገር፣ ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ ማሻሻያዎችን እንደሚተገብር ገልጸዋል።

በከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ግብይት ድጋፍና ክትትል የሥራ ሂደት ተወካይ አቶ ሰይድ መሃመድ፤ ለግብር ከፋዮች ስለ አገልግሎቱ አጠቃቀም በቂ ስልጠናና ተከታታይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


የቅርንጫፉ የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ክፍያ አሰባሰብና ክትትል ቡድን አስተባባሪ ተወካይ አቶ ኢድሪስ መሃመድ በበኩላቸው፣ አዲሱ የዲጂታል ሥርዓት ተቋማዊ አፈጻጸምን ከማሳደግና ሥራዎችን ከማቅለል አንጻር ሰፊ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።


የቅርንጫፉ ተገልጋዮችም በአዲሱ አሠራር መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ታምራት አብራሃም በሰጡት አስተያየት አዲሱ የኦንላይን ሥርዓት ረጅም ሰልፍን ያስቀረና ተገልጋዩ በቤቱ ሆኖ ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት እንዲችል ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አዲሱ አሠራር በሥራቸውና በድርጅታቸው ላይ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን እንዳስገኘላቸው የገለጹት ደግሞ አቶ ሙልጌታ ተሻለ ናቸው፡፡

አቶ እስጢፋኖስ ብርሃኔ በበኩላቸው የዲጂታል አሠራሩ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል ይደርስባቸው የነበረውን ከፍተኛ እንግልት ሙሉ በሙሉ ማስቀረቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026