የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ባቡር መስመር ጥገናን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው

Jul 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ኮምቦልቻ፤ ሰኔ 23/2018 (ኢዜአ)፡- የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ባቡር መስመር ፕሮጀክት ጥገናን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ ።

የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በቅርቡ የጥገና ስራ የተጀመረውን የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክትን ዛሬ ጎብኝተዋል።


የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ህሊና በላቸው እንደገለፁት፣ ባቡር መስመሩ የወጭና ገቢ ንግድን በማሳለጥ ለአገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረውን የባቡር መስመር የጥገና ስራን በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ ለአገልግሎት ለማብቃት በተለየ ቅንጅት እየተሰራ መሆኑንገልጸዋል።

በዛሬው እለትም የኮርፖሬሽኑ የስራ አመራር የጥገና ስራው ያለበትን ደረጃ በአካል ተገኝቶ በመመልከት የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡም የባቡር መስመር ፕሮጀክቱን ሃብትና ንብረት በመጠበቅና በግንባታ ስራውም የራሱን አሻራ በማሳረፍ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።


የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጅነር ብርሃኑ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የፕሮጀክቱ ጥገና ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ መንግስት በተለየ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

የፕሮጀክቱ ጥገናም በቀጣይ የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቃቃትና ለአገር እድገት መሰረት በመሆን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ እንደሆነም አብራርተዋል።

አዋሽ- ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ባቡር መስመር ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዳንኤል ኪዳነማሪያም በበኩላቸው የፕሮጀክቱ የጥገና ስራ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።


ከአዋሽ -ኮምቦልቻ -ሃራ ገበያ 392 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ፕሮጀክት በአራት አቅጣጫ የጥገና ስራው እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው የካምፖች፣ የሀዲድ መስመርና የባቡር ጥገና እየተካሄደ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ጠግኖ ለማስረከብ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

በጉብኝቱ የኮርፖሬሽኑና የኮምቦልቻ ከተማ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026