የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ዩኒቨርሲቲው በሽታን የሚቋቋሙ ዝርያቸው የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን ለአካባቢው ማህበረሰብ እያሰራጨ ነው

Jul 6, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅማ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሽታን የሚቋቋሙና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያቸው የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን ለአካባቢው ማህበረሰብ እያሰራጨ መሆኑን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ዘርፈ ብዙ የምርምር ሥራዎችን እንደሚያከናውን ጠቅሰው፣ ከእነዚህ መካከል የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን በማዘጋጀት ለሕብረተሰቡ ማሰራጨት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለዘንድሮው ክረምት በዩኒቨርሲቲው ለአረንጓዴ ዐሻራ ከተዘጋጁትና የተለያየ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ካላቸው ችግኞች በተጨማሪ፣ አንድ ሚሊየን በሽታን የሚቋቋሙ የተሻሻሉ የቡና ችግኞች እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

የቡና ችግኞቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ምርት መስጠት የሚችሉ በመሆናቸው፣ ከአርሶ አደሩ በተጨማሪ ቡናን ለሚያለሙ ባለሀብቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በተጨማሪም ከ500 ሺህ በላይ የፍራፍሬ፣ የውበት እና ሌሎች የሀገር በቀል ዕፅዋት ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንም ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው የፍራፍሬ ምርትን ይበልጥ ለማስፋፋትና ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በሁለት ወረዳዎች ላይ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም አክለዋል።

በዩኒቨርሲቲው የግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ ዲን ሰለሞን ቱሉ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የቡና ምርት ሊያሳድጉ የሚችሉ የተሻሻሉ ዝርያዎች በሦስት የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች እየተዘጋጁ ለማኅበረሰቡ ሲሰራጩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም፣ በተለይም በዩኒቨርሲቲው ግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ የምርምር ተቋም አማካኝነት ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው የግብርና ሥራውን የሚያስፋፋው የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን በስፋት በመጠቀም እንደሆነ ገልጸው፣ በዘንድሮው ዓመት ብቻ 120 ቶን የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን አክለዋል።

ከዩኒቨርሲቲው የቡና ችግኝ ከወሰዱ ባለሀብቶች መካከል አቶ ግደይ በርሄ እንደገለጹት በራሳቸው ከሚያዘጋጁት በተጨማሪ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ከዩኒቨርሲቲው በመውሰድ እያለሙ ይገኛሉ።

የቡና ችግኙን በ350 ሄክታር መሬት ላይ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመው በልማቱም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠራቸውን አክለዋል።

ከዩኒቨርሲቲው የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በመውሰድ በሰፊው እያለሙ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው ተጠቃሚ አቶ ፈለቀ ሌንጮ የቡና ችግኞቹ በብዛትና በጥራት ምርት የሚሰጡ ስለሆኑ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን በተሻለ ሁኔታ እያሳደገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026