🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወርቅ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 5 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የማስገኘት አቅም ፈጥሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በሰጡት የወርቅ እመርታዊ ውጤቶች ማብራሪያቸው፤ ከ1984 እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ በሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ በድምሩ የኢትዮጵያ ወርቅ ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን አስታውሰዋል።
በአንድ ዓመት ውስጥ ግን ከወርቅ ወጪ ንግድ 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማገኘት የተቻለበትን አቅም መፍጠሩን አስታውቀዋል።
በአንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገበው እመርታ የ27 ዓመታት ሥራን እንደሚበልጥ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ዓይነቱ ስኬት እውነተኛ የዕድገት ማረጋገጫ መሆኑን አስምረውበታል።
በኢትዮጵያ ቁጥር ሳይሆን የሚጨበጥና የሚዳሰስ የሚታይም ዕድገት ነው እየመጣ የሚገኘው ብለዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026