🔇Unmute
ወልቂጤ፤ሐምሌ 9 /2018 (ኢዜአ)፦በጉራጌ ዞን ለእደ-ጥበብ ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደገው መምጣቱን በዘርፉ የተሰማሩ ሙያተኞች ገለጹ።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ በበኩሉ ዘርፉ ካለው ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ ባለፈ የቱሪዝም መስህብን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ ማበርከቱን አስታውቋል።

በዞኑ የባህል አልባሳት፣ የሸክላ ውጤቶችና የቤት መገልገያዎችን ጨምሮ በተለያዩ የእደ-ጥበብ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ የአካባቢው አምራቾችና ሻጮች በተሰማሩበት ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
የታንቶስ ባህላዊ እቃዎች ኢንተርፕራይዝ ሰብሳቢ ወይዘሮ ቅድስት ትዕዛዙ እንዳሉት፣ የጉራጌ ባህል መገለጫ የሆኑ የእደ-ጥበብ ምርቶች ጥራት እንዲጨምር በስልጠናና በተለያየ መንገድ የተደረገላቸው ድጋፍ ሥራቸውን በማሻሻል የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡

ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ከተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በተጨማሪ በኤግዚቢሽንና በቱሪስቶች መዳረሻ አካባቢዎች የገበያ ቦታ መመቻቸቱ ምርቶቻቸውን ለጎብኚዎች እና ለሸማቾች በቀጥታ እንዲያቀርቡ ማገዙን ተናግረዋል።
የጉራጌን ማህበረሰብ ጥበብና ታሪክን የሚያንጸባርቁ የቤት ውስጥ መገልገያዎችንና ጌጣጌጦችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን ገልጸዋል።
የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም የእደ ጥበባት ክፍል ተጠሪ አቶ አብድልከሪም ጀማል በበኩላቸው እንዳሉት፤ በተቋሙ የሚከናወነው የእደ ጥበብ ስራ ከቱሪዝም ልማቱ ጋር መተሳሰሩ በኢኮኖሚ በተሻለ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል።

መንግስት ለእደ-ጥበብ ዘርፉ ድጋፍ ማድረጉ ምርቶቻቸውን በተሻለ ጥራት ለማምረት ከማስቻሉ በተጨማሪ የማህበረሰቡን ታሪክና ባህል በምርቶቻቸው ለማስተዋወቅ እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው፤ የእደ-ጥበብ ዘርፍ የአካባቢውን ባህላዊ እሴት ጠብቆ ለማቆየት እና ለቱሪዝም መነቃቃት ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል።

ወደ ዞኑ ለሚመጡ ቱሪስቶች የእጅ ሥራዎችን በማቅረብ በዘርፉ ለተሰማሩ ግለሰቦችና ለአካባቢው ተጨማሪ ገቢ እየተገኘ መሆኑን ገልጸው፣ የእጅ ሥራዎቹ የዞኑን በጎ ገጽታ በተሻለ ለማስተዋወቅ ጭምር ያግዛሉ ብለዋል።
በዞኑ የዕደጥበብ ምርቶችን ይበልጥ ተወዳዳሪ ለማድረግና ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በስልጠና፣ በፋይናንስ እና በገበያ ትስስር የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመልክተዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026