የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ከ22 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ማሳ በመስኖ እየለማ ነው

Jan 13, 2025

IDOPRESS

ሀዋሳ፤ ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡- በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ከ22 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ኩታ ገጠም ማሳ በመስኖ እየለማ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።

የአርሶ አደሩን ገቢ ማሳደግና ገበያን ማረጋጋት ታሳቢ አድርጎ እየተከናወነ ካለው የመስኖ ልማት ሥራ ከ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱ ተመላክቷል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብሩክ ሰለሞን ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በዞኑ በበጋ መስኖ ከ22 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ማሳ በተለያዩ ሰብሎች እየለማ ሲሆን ለስኬታማነቱም በግብአት አቅርቦትና በተለያየ መንገድ ድጋፍ እየተደረገ ነው።

የመስኖ ልማቱ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ገበያን የማረጋጋት ግብ እንዳለው ጠቁመው፣ በመጀመሪያ ዙር የመስኖ ልማት ሥራ የተለያዩ አትክልቶችን የማልማት ስራ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ገጠር ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ አሰፋ ፎና በበኩላቸው በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ዘመናዊ መስኖ፣ ጥልቅ ጉድጓድ፣ ወንዞችን በመጥለፍና ባህላዊ ኩሬን በመጠቀም የመስኖ ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በዋናነት ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን፣ ድንች፣ ቃሪያ እና ሽንኩርት በ145 ክላስተር በኩታ ገጠም የማልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።

የመስኖ ልማቱ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ገበያን ለማረጋጋትና የሥራ ዕድል መፍጠር በሚያስችል መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ በልማቱ ከ76 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ ብለዋል።

ከመስኖ ልማቱ ከ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን አቶ አሰፋ ጠቁመዋል።

በዞኑ ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ጃራሂኒኤሳ ቀበሌ በ3 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ አራት ሆነው በኩታ ገጠም እያለሙ መሆናቸውን የገለጹት አርሶ አደር ታደሰ ጌታሁን በበኩላቸው፣ በዓመት ሦስት ጊዜ ምርት እንደሚሰበስቡ ተናግረዋል።

በተያዘው የበጋ መስኖ በዋናነት እያለሙት ካለው ቲማቲም፣ ጎመንና ቃሪያ የተሻለ ገቢ ለማግኘት ልማቱን አስፋፍተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በጋሎአርጊሳ ቀበሌ ከቤተሰቡ ጋር በመስኖ ልማት የተሳተፈው ወጣት ተመስገን ሽመልስ በበኩሉ፣ በአሁኑ ወቅት በመስኖ ያለሟቸው የተለያዩ አትክልቶች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በመስኖ ልማቱ ከ50 ለሚበልጡ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን የተናገረው ወጣቱ፣ በመስኖ ልማቱ የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን ተስፋ ማድረጉንም ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025