ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ።
በፕሮጀክቱ በመኩይ ወረዳ የተገነባው የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።
በቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የጋምቤላ ክልል አስተባበሪ ቤል ቢቾክ(ዶ/ር) በዘንድሮው በጀት ዓመት በፕሮጀክቱ በተለይም የትምህርትና የጤናን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም እስካሁን የሰባት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቆ ለአገልገሎት እንዲበቁ መደረጉን ጠቅሰው በዛሬው እለት የተመረቀው የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም ቀሪ ፕሮጀከቶችን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት የሚደረግ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የመሰረተ ልማት አማካሪ ፒተር አማን፤ የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የክልሉን ልማትና የህዝቡን ተጠቀሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው እለት የተመረቀውን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት በርካታ የማህበራዊና ኢኮኖያዊ ፋይዳ ያላቸውን ሰው ተኮር ፕሮጀከቶችን በማጠናነቅ አገልግሎት አንዲሰጡ ማድረጉንም አስታውሰዋል።
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ብሩ በበኩላቸው የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቱ የክልሉን የእንስሳት ሃብት የስጋና የወታት ተዋጽኦ ምርት ለማሳደግና የተሳለጠ የግብይት ስርዓት እንዲዘረጋ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።
በፕሮጀክቱ ከአራት በላይ የእንስሳት 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ የግብይት ማዕከል፣ የወተትና የማር ማቀነባበሪያና ሌሎች ዘርፉን የሚያግዙ የመሰረተ ልማት አውታሮች መገንባቱን ጠቁመው ለበርካታ ወጣቶችም የስራ እድል መፍጠሩን ጠቅሰዋል።
በጋምቤላ ክልል የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በተመረጡ ዘጠኝ ወረዳዎች እየተተገበረ መሆኑ ታውቋል።
የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በቆላማ አካባቢዎች ያለውን ፀጋ በመጠቀም በተለይም የአርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮችን የአኗኗር ዘይቤና የህይወት መንገድ የተቃና ለማድረግ የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025