የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል

Feb 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ መቻሉን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ገለጹ።

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓቱን ለማዘመን የዘርፉን ተዋንያን ማብቃት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ትምህርት መስጫ /e-learning/ መተግበሪያ በይፋ ስራ አስጀምሯል።

የኤሌክትሮኒክ ትምህርት መስጫ መተግበሪያው ሸማቾችና አቅራቢዎች በበይነ መረብ እርስ በርስ በመማማር በእውቀትና በውድድር ላይ የተመሰረተ ግዥ መፈፀም ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

የመንግሥትና የአቅራቢዎችን ጊዜና ገንዘብ በመቆጠብ ቀልጣፋና ዘመኑን የዋጀ የግዥ ስርዓት ገቢራዊ ለማድረግ የታለመ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የግዥ እቅድና የፕሪፎርማ ግዥ ጨረታ ሰነድ አዘገጃጀት፣ የኮንትራት አያያዝና አስተዳደርን ባሉበት ቦታ ሆኖ ለመማር የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በ www.elearning.ppa.gov.et ወይም elearning.ppa.gov.et በመግባትና በመመዝገብ የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘትና መማር እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) መተግበሪያውን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የመንግሥት የግዥ ስርዓት በዲጂታል አሰራር እየዘመነ መጥቷል ብለዋል፡፡

የመንግስት አገልግሎትና የፋይናንስ ስርዓቱ በዲጂታል የታገዘ ዘመናዊና ተደራሽ በመሆኑ በዘርፉ ትርጉም ያለው ለውጥ መመዝገቡንም ገልጸዋል።

በመሆኑም የመንግስት የግዥ ስርዓት ከየትኛውም የዓለም ክፍል ያለን ተወዳዳሪ በእኩልነት በማሳተፍ ግልጽነት እና የሀብት ብክነትን ማስቀረት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

የፋይናንስ ስርዓቱ እና የህዝብ አገልግሎቱ ዲጂታላይዝ በመደረጉ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የግዥ ስርዓቱን ለማዘመን ዛሬ ይፋ ያደረገው የኤሌክትሮኒክ ትምህርት መስጫ መተግበሪያ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

መተግበሪያው በራስ አቅም የለማ፣ የኢትዮጵያን ብዝሀነትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት መሰረት ያደረገ ቋንቋ የያዘ እንዲሁም በመረጃ የበለጸገ መሆኑ ልዩ ያደረገዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መድረስ ከሚገባን አንፃር ተገልጋዩ የመንግስትን ህግና አሰራር አውቆ ስራውን በተሳለጠ መንገድ እንዲሰራ ያስችላልም ነው ያሉት፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው፤ የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ጊዜና ገንዘብን በመቆጠብ የተቀላጠፈ የግዥ ስርዓት መፍጠር አስችሏል ብለዋል፡፡

የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓትን በተሟላ ሁኔታ ገቢራዊ ለማድረግ የተቋማትና የባለሙያዎች የእውቀት ክፍተት እንደነበር ጠቅሰው፤ በመተግበሪያው አማካኝነት ባሉበት ቦታ ሆነው መረጃውን ማግኘት የሚችሉበትን እድል መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025