
አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2017(ኢዜአ)፦ በሶማሊያ ፓርላማ ዛሬ ከፍተኛ ብጥብጥ ተከስቷል።
የሶማሊያ መንግስት አካሄድን የተቃወሙ የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ቁጣቸውን በፓርላማ ውስጥ ሲገልጹ ታይተዋል።
የሶማሊያ ፓርላማ ባወጣው መግለጫ የሀገሪቱ መንግሥት የሶማሊያ ጦር አልሸባብን ከመዋጋት ይልቅ በጎሳ ክፍፍል እንዲወጠር በማድረግ የያዛቸውን ቦታዎች እንኳ እንዳያስተዳድር አድርጓል ብሏል።
በሀገሪቱ ሙስና ስር እየሰደደ ከመምጣቱም ባሻገር መንግስት ጦሩን ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጠቀመ መሆኑንም ነው ፓርላማው በመግለጫው ያስታወቀው።
ይህም በሀገሪቱ የጎሳ ክፍፍል እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑንም አስታውቋል።
ከሶማሊያ ህገ መንግስት ባፈነገጠ መልኩ የሀገሪቱ መንግስት የክልላዊ አስተዳደሮችን መብቶች እየተጋፋ መሆኑንም እንዲሁ።
የሶማሊያ መንግስት ሶማሊያውያንን በጎሳ ለመከፋፈል የሚያደርገው ሙከራ በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል።
የሀገሪቱ መንግስት ከመሰል አደገኛ አካሄዱ ካላቆመም ሶማሊያ የመፍረስ አደጋ እንደሚገጥማት የፓርላማ አባላቱ ባወጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026