
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2017(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሰሞኑን እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥና ንዝረት በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ጋር ተወያዩ፡፡
ከንቲባዋ ሰሞኑን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ስለተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ንዝረት እንዲሁም አጠቃላይ ስርጭቱን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም እንዲሁም ከጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከመጡ ምሁራን ጋር ተወያይተናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

በውይይታችንም ምሁራኑ ጥናቶችን ያቀረቡልን ሲሆን ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት በአዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት በአፋር እና አካባቢው እያጋጠመን ካለው የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳ የመሬት ንዝረት እያጋጠመ መሆኑን ገልፀው ንዝረቱ ሲያጋጥም መደናገጥ እና መረበሽ ሳያስፈልግ በባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን በመከታተል መረጋጋት እንደሚገባ አስረድተውናል ብለዋል።
ቢሆንም ከተማችን አዲስ አበባ ወደፊት ተጋላጭነት ያላት በመሆኑ የምንችለውን ተገቢውን ጥንቃቄ ከወዲሁ ማድረግ እንዲያስችል ለአንዳንድ ቅድመ ጥንቃቄ የሚረዱ ጥናቶችን ለማድረግ የባለሙያዎች ግብረ ሀይል በማደራጀት በጋራ ለመስራት ተስማምተናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026