
መቱ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- በኢሉአባቦር ዞን በአርሶ አደሮች ተሳትፎ ከ11 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጫሊ ለኢዜአ እንደገለጹት የተፈጥሮ ማዳበሪያው እየተዘጋጀ ያለው በዞኑ ዘጠኝ ወረዳዎች ነው።
የተፈጥሮ ማዳበሪያው በአካባቢ ከሚገኙ ግብአቶች እንደሚዘጋጅ ጠቅሰው ይህም የአፈር ለምነትና እርጥበት በመጨመር ምርታማነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል አስረድተዋል።
ለስራው ስኬታማነት በወረዳዎቹ የ'ቨርም ኮምፖስት' ማዘጋጃ ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን ስራውም በግብርና ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ተደግፎ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ የመሬት ለምነትንና አርጥበትን ለረዥም ጊዜ ጠብቆ በማቆየት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ የተሳታፊ አርሶ አደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም አብራርተዋል።

ከዞኑ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ታደሰ አምቢሳ እንደሚሉት የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት ለመኽር እርሻ ልማት በማዋል ምርታቸውን በማሳደግ ላይ ናቸው።
ሌላኛው አርሶ አደር አዲሱ ተፈሪ በበኩላቸው ከፍግና ከዕፅዋት ብስባሽ የሚያዘጋጁት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለአፈር ለምነት ከፍተኛ ጠቀሜታ ስላለው በስፋት እያዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅትም በቀያቸው ለመጪው መኸር እርሻ የሚያስፈልጋቸውን የተፈጥሮ ማዳበሪያ የማዘጋጀት ስራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።
አርሶ አደር ጌታቸው ጊጆ በበኩቸው፣ የማሳቸውን ለምነት በመጠበቅ ምርትና ምርታማነታቸውን ለመጨመር የተፈጥሮ ማዳበሪያ የማዘጋጀት ልምድ ማዳበራቸውን ይገልጻሉ።
በተለይ በወረዳው ከተሰራው የቨርም ኮምፖስት ማምረቻ ማዕከል የተሻለ ልምድና ተሞክሮ እየቀሰሙ መሆናቸውን ገልጸው ይህም ይበልጥ በዝግጅቱ እንዲቀጥሉበት አቅም እንደፈጠረላቸው አስረድተዋል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ቀደም ሲል ለሰው ሰራሽ ማዳበሪያ መግዣ ሲያወጡ የነበረውን ወጪ በግማሽ ለመቀነስ እንዳስቻላቸው ነው አርሶ አደሮቹ የተናገሩት።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026