
አዲስ አበባ፤ጥር 3/2017(ኢዜአ)፦ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ የሳይበር ባለሙያ ማፍራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለጸ።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሰመር ካምፕ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን 337 ባለተሰጥኦ ታዳጊዎች አስመርቋል።
የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ በዚሁ ጊዜ፥ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ብቃት ያለው የሳይበር ባለሙያ በብዛትና በጥራት ማፍራት ያስፈልጋል ብለዋል።
አስተዳደሩ ከመላ ኢትዮጵያ የተወጣጡ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊዎችን በሳይበርና ተያያዥ ዘርፎች እያበቃ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ተለዋዋጭ የቴክኖሎጂ ዕድገትን የሚመጥንና የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ የማፍራት ጥረቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ነው ያነሱት።
በአስተዳደሩ የሳይበር ማዕከል ዳይሬክተር ቢሻው በየነ በበኩላቸው፥ ከአገራዊ ለውጡ በኃላ ለባለተሰጥኦ ወጣቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ማዕከሉ ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ የሚሰጠው ስልጠና ተደራሽነት ለማስፋት ጥረት እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
የመከላከያ ሳይበር ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ(ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያን የሚመጥን ጠንካራ የሳይበር ባለሙያ ግንባታ በሁሉም ዘርፎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የትምህርትና ሌሎች ተቋማትም የባለተሰጥኦ ወጣቶችን አቅም መጠቀም ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ነው ያነሱት።
ከሰልጣኞቹ መካከል ዳዊት ከተማና ዳንኤል ቢፍቱ በበኩላቸው በስልጠናው መሰረታዊ የዲጅታል ዕውቀት ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።

ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤቶችን በማፍለቅ አገርና ህዝባቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
በተመሳሳይ አስተዳደሩ የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በቅዳሜና እሁድ የስልጠና ፕሮግራም ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ 40 ተማሪዎች መስጠት ጀምሯል።
ስልጠናውን ለመውሰድ ያለው ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱም ነው የተገለጸው።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026