የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች የቱሪዝም ሀብቶችን ለማስተዋወቅና ለማስጎብኘት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- በመጪው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለሚሳተፉ እንግዶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ማስተዋወቅና ማስጎብኘት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም፣ 46ኛው የሕብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ደግሞ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በህብረቱ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሀገራት መሪዎች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የአለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።


ይህን መነሻ በማድረግ የቱሪዝም ሚኒስቴር ለጉባኤው ታዳሚዎች የቱሪዝም ሀብቶችን ለማስተዋወቅና ለማስጎብኘት እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዝግጅቶችን ለኢዜአ ገልጿል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ አለማየሁ ጌታቸው ኢትዮጵያ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ እምቅ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ያሏት እና በልዩ ልዩ ባህሎች የታደለች ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።

እነዚህን እምቅ የቱሪዝም ሀብቶች በጉባኤው ላይ ለሚሳተፉ እንግዶች ማስተዋወቅና ማስጎብኘት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

እየተከናወኑ ካሉ ዝግጅቶች መካከል አስጎብኚ ድርጅቶች የጉብኝት ፓኬጆችን ቀድመው እንዲያዘጋጁ ማድረግ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።


አዳዲስ የተገነቡ እና ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን በቴክኖሎጂ በተደገፈ መልኩ ለተሳታፊዎች እንዲቀርቡ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የጉባኤውን ምቹ አጋጣሚ በአግባቡ ለመጠቀም ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ እንገደሚገኝ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ አለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ስብሰባዎች እየተስተናገዱ መምጣቱ የሀገሪቱን የቱሪዝም ሀብቶች እንዲጎበኙ መልካም እድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል።

ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚመጡ እንግዶችንም በአግባቡ በለማስተናገድ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025