የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የተቀዱ 77 ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር ተችሏል</p>

Jan 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡-ባለፉት ስድስት ወራት በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የተቀዱ 77 ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።

ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራ ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን የሚፈጠሩ ቴክኖሎጂዎች ደግሞ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በማኑፋክቸሪንግና ዘርፎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ሊፈቱ ይገባል።


በዚህ ረገድ ቢሮው ከተሰጠው ተልዕኮ አኳያ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት የማሸጋገር ስራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

በቢሮው የቴክኖሎጂና የኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ መሃመድ ልጋኔ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 77 ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት ወደ ኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር መቻሉን ጠቅሰዋል።


ቴክኖሎጂን ከመቅዳት ባለፈ ለኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር ውጤት እንዲመዘገብ የተሻለ ስራ መሰራቱን አስታውቀዋል።

በዚህም በማምረቻ 26 ፣ በምርት ቴክኖሎጂ 40 ፣ በሀገር በቀል ቴክኖሎጂ 6፣ በአይሲቲ 13 በድምሩ 85 ቴክኖሎጂዎችን የመቅዳት ስራ ተሰርቷል ነው ያሉት።

ኢንተርፕራይዞቹ በተደረገላቸው ድጋፍና ክትትል በአዲስ መንገድ ማምረት በመቻላቸው የተሻለ ውጤት ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።

በቀጣይ ስድስት ወራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ምክትል ቢሮ ሃላፊው የተናገሩት።

የተቀዱ ቴክኖሎጂዎችን በአውደ ርዕዮች ላይ በማቅረብ ኢንተርፕራይዞቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026