የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ሪች ዲጂታል በኢትዮጵያ የአይሲቲ ዘርፍ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ</p>

Jan 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡-የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋም ሪች ዲጂታል (REACH Digital) በኢትዮጵያ በዘርፉ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ገሰሰ (ዶ/ር) ከሪች ዲጂታል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ኮሚሽነሩ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ጨምሮ ኢትዮጵያ በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የግሉ ዘርፍ በሀገሪቷ ኢኮኖሚ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ሪፎርሞችን እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የአይሲቲውን ዘርፍ የሚያሳድጉ ጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀፎች መኖራቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ፥ፖሊሲው መንግስት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትምንት ለመሳብ እየተገበራቸው ከሚገኙ ኢኒሼቲቮች ጋር የተቆራኘ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል፣ ኢነርጂ፣ ኢንተርኔት እና የአይሲቲ ፓርኮችን ጨምሮ የመሰረተ ልማቶች አቅርቦት እንዲሁ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የገበያ አቅም እንዳላት አስረድተዋል።

ሪች ዲጂታል ምቹ እድሎቹን በመጠቀም በዘርፉ እንዲሰማራ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋም ሪች ዲጂታል (REACH Digital) ተወካዮች በበኩላቸው ተቋሙ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ለአይሲቲ ልማት አመቺ ምህዳር እንዳለ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026