የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>አዲስ ያስገባናቸው ድሮኖች ከከተማ ፀጥታ ቁጥጥር ባሻገር የቦርደር ሴኪዩሪቲን የኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በቀላሉ መቆጣጠር የምንችልበትን ዕድል ይፈጥራሉ - ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል</p>

Jan 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2017(ኢዜአ)፡- አዲስ ያስገባናቸው ድሮኖች ከከተማ ፀጥታ ቁጥጥር ባሻገር የቦርደር ሴኪዩሪቲን የኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በቀላሉ መቆጣጠር የምንችልበትን ዕድል ይፈጥርልናል ሲሉ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ።


ኮሚሽነር ጀነራሉ በዋናው መስሪያ ቤት የተደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል(UAV Simulation Training Center) መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ኮሚሽነር ጀነራሉ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ፖሊስ ውስጥ የተዋወቀው የድሮን ቴክኖሎጂ ማዕከል ወጣት የፖሊስ ኦፊሰሮቻችን የቴክኖሎጂ ስልጠና አግኝተው በፖሊስ ውስጥ የተሻለ የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት የተፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል።

አሁን ላይ በተቋሙ ያለው የድሮን አቅም በፖሊስ የወንጀል መከላከል ሰርቪላንስ እና የምርመራ ስራ ከፍተኛ እገዛ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡


በፖሊስ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፖሊስ በዘመኑ እንደዚህ አይነት ቴክኖሎጂዎችን ታጥቆ አያውቅም ያሉት ኮሚሽነር ጀነራሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በሪፎርሙ አሁን ላይ ከአፍሪካ አምስቱ ምርጥ የፖሊስ ተቋማት ውስጥ ለመግባት እያደረገ ያለውን ጥረት በሚያግዝና ለአፍሪካ ወንድሞቻችንም ልምድ እና ተሞክሮ ማስተላለፍ በሚያስችል መልኩ እየተደራጀ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በሪፎርሙ መንግስት ለፖሊስ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የሀገራችን ፖሊስ ዘመናዊ ትጥቆች እንዲኖሩትና ሰብዓዊ መብትን ባከበረ መልኩ የወንጀል መከላከል ስራዎቻችንን ለመስራት በሚያስችል አቅሙን እያሳደገ ነው ብለዋል፡፡


እንደአዲስ አበባ ያሉ ትላልቅ ከተሞችን ፓትሮል ለማድረግ የእግረኛ ፖሊስ ሠራዊትን ከድሮን ፓትሮል ጋር በማቀናጀት እና በማዋሀድ የወንጀል መከላከል ስራችንን እያቀላጠፍን የምንሰራበት እድል ከመፍጠር ባለፈ አድማዎች ሲያጋጥሙ በተደራጀና በጠንካራ ሠራዊታችንና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘን በቀላሉ ችግሮችን መቆጣጠር የሚያስችል አቅም ፈጥረናል ነው ያሉት፡፡

እንደ አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ያሉ መድረኮች ሲኖሩ ለተወሰነ ጊዜ መንገዶችን ዘግቶ ቪአይፒዎችን ማስተናገድ የሚያስችል የራሱ የሆነ ኮማንድ ኮንትሮል ያለው ዘመናዊ Road block ተሸከርካሪም በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራ እንዲጀምር መደረጉን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026