አዳማ ፤ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት አመቱ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በስፋት እየተዘጋጀ በበጋ መስኖ ልማት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ከድር ለኢዜአ እንደገለጹት የአፈር ለምነትን ለመጨመር የተፈጥሮ ማዳበሪያ የማይተካ ሚና አለው።
በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው በአዘገጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ የአርሶ አደሮችን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል።
በዚህም በጀት ዓመቱ 250 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት የታቀደ ሲሆን በእስካሁኑ ሂደት ከ163 ሚሊዮን ሜትር ኩዩብ በላይ መደበኛና ቫርሚ ኮምፖስት ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል ብለዋል።
በክልሉ ባለፉት ዓመታት 287 የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጂያ ማዕከላት መገንባታቸውን ጠቁመው እስካሁን በተሰራው ስራ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በግብርና ምርትና ምርታማነት እድገት ላይ በጎ ተጽእኖ እያሳደረ መምጣቱን አስታውሰዋል።
በቢሮው የአፈር ለምነት ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ለገሰ በበኩላቸው በክልሉ ከባለፈው ነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ የዘንድሮው የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ ከመደበኛ ኮምፖስት በተጨማሪ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቨርሚ ኮምፖስት እንዲሁም ከባዮጋስ ተረፈ ምርት የተፈጥሮ ማዳበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በበጀት ዓመቱ የተዘጋጀው የተፈጥሮ ማዳበሪያ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ በክልሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ግብርና ምርትና ምርታማነት እድገት እንዲጨምር አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025