ሮቤ፤ ጥር 9/2017 (ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ከ32 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ ያባዛውን ምርጥ ዘር እየሰበሰበ መሆኑን አስታወቀ።
የኢንተርፕራይዙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የቦርድ አባላት በባሌ ቅርንጫፍ ሥር የሚገኙ የሮቤና ሲናና የእርሻ ማሳዎች የሰብል ስብሰባ ሂደት ያለበትን ደረጃ ተመልክቷል።
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጫላ አበበ በወቅቱ እንደገለጹት ኢንተርፕራይዙ የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግርን ለማቃለል የሚያግዙ ሥራዎችን እያካሄደ ነው።
በዚህም ኢንተርፕራይዙ ከ32 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ ያባዛቸው የሰብል ዝርያዎች ከምርምር ተቋማት የተለቀቁ እንደሆኑ ጠቁመዋል።
እየተሰበሰቡ ከሚገኙት የሰብል ዝርያዎች መካከል የዋግ በሽታን በመቋቋም የተሻለ ምርት የሚሰጡ የስንዴና የቢራ ገብስ ዘር እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
በተለያዩ ዞኖችና ስነ-ምህዳር ውስጥ ከሚባዙት የተለያዩ የሰብል አይነቶች ከ 870 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ምርጥ ዘር ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
አቶ ጫላ እንዳሉት፣ የመስክ ምልከታው ዓላማ የሰብል ስብሰባ ሂደትን በመገምገም የዘር ብጠራና ስርጭትን በወቅቱና በሚፈለገው ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ መሆኑን አመልክተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025