የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በምዕራብ ጎንደር ዞን  የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ  ሥራ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እድገት  የጎላ አስተዋጽኦ አበርክቷል

Jan 22, 2025

IDOPRESS

መተማ ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ጎንደር ዞን ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እድገት የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በዞኑ መተማ ወረዳ ኩመር አፍጥጥ ቀበሌ የ2017 ዓመት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ማስጀመሪያ መረሃ ግብር ዛሬ ተካሄዷል።

በዚህ ወቅት የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ጤናው ፈንታሁን እንደተናገሩት፤ ቀደም ሲል በተከናወነ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎች በደን ይዞታዎች ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አስችሏል።

በተለይ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ በርካታ ምርት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማቅረብ እንዳስቻለ አመልክተዋል።

በተለይም ማንጎ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ሙዝና ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች በተቀናጀ ተፋሰስ በማልማቱም የአካባቢው ማህበረሰብ ከምግብ ፍጆታ አልፎ ከምርት ሽያጭ ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል።

በለሙ ተፋሰሶች የንብ ማነብ፣ የእንስሳት ማድለብ፣ በጎለበቱ ምንጮችና ወንዞች መስኖ ልማት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዓመትም ያለፈውን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት በ91 ተፋሰሶች ውስጥ አንድ ሺህ 500 ሄክታር በላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ለማከናወን ዛሬ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

በዚህም ከ35 ሺህ በላይ ህዝብ ለማሳተፍ ታቅዶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅሰው፤ ለቀያሽ አርሶ አደሮች ስልጠናና የመስሪያ መሳሪያ ልየታ መከናወኑንም አስረድተዋል።

በሥራው እየተሰታፉ ካሉት መካከል የአካባቢው አርሶ አደር እሸቱ ይስማው በሰጡት አስተያየት፤ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ልማት ሥራው የተቦረቦሩ ስፍራዎች በማልማት ተጠቃሚ መሆን እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በለሙት ተፋሰሶች ለከብቶች መኖን ማልማት መጀመራቸውን ጠቅሰው፤ የተፋሰስ ልማት ስራው በየዓመቱ በጉጉት የሚጠብቁት መሆኑን አመልክተዋል።

ሌላኛው አርሶ አደር ከፋለ ይግዛው በበኩላቸው፤ በለሙት ተፋሰሶች ላይ አትክልትና ፍራፍሬ በመትከል መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ማንጎ፣ ፓፓያና ዘይቱን በማልማት ከፍጆታቸው አልፎ ለገበያ ማቅረብ መጀመራቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ሙዝና ሌሎች የቆላ ፍራፍሬዎችን ለማልማት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ያስገኘው ጠቀሜታ ለማስቀጠልም እየተዘጋጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቀደም ሲል በለሙ 42 ተፋሰሶች አንድ ሺህ 200 ለሚደርሱ ዜጎችን የስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025